Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፳~ ( 220) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 #ራስ አምባ 'እሱ ቅቤ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳~ ( 220)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
#ራስ አምባ
"እሱ ቅቤ ነው አንድ ጊዜ ተገፍቶ የወጣ"አለች አትጠገብ። የግንባሯ ቆዳ ተሸብሽቦ የፊት ፀጉሯ ውስጥ ተደብቋል። በንግግሯ ውስጥ ቁጭት ፀፀት እንደ ስምንት ወር ፅንስ ይገላበጣል። የተቆጠበ የተመጠነች ንግግር ነበረች። ሌላ አንድም ቃል አልተነፈሰችም። ከወትሮው ወጣ ያለ አነጋገር ነበር። ማለፊያ የእናቷ ቃል አጥንቷን ሰርስሮ ዘልቆት የገባው ይመስላል። "ምን ሆነሽ ነው እታተዬ እንደዚህ የምትይው?"አለች ማለፊያ የአትጠገብን ጉንጭ በእጆቿ እየዳበሰች። "እንዳይረፍድባችሁ ልጄ! እንደኔ የማትመልሱት ነገር እንዳይገጥማችሁ ፍጠኑ። እኔ ልጅ ሆኜ በማይሆን እልህ እናንተን እዚህ ገደል አብሬ አስገብቻችኋለሁ። እንግዲህ ለዚህ በደሌ በምድርም በሰማይም እቀጣበታለሁ። እናንተ ግን ጊዜ አላችሁ ንስሃ የምትገቡበት ኃጢያታችሁን በንስሃ የምታጥቡበት ጊዜው አሁን ነው። አሁን ቀዳማዊን እርሱት። እሱ እረስቶናል። የራሱን ቤተሰብም መስርቷል። ሊያገባ ነው። ሕይወቱ ውስጥ የለንም። እሱም እስከ ወዲያኛው ከበደላችን ጋሬ አስፈንጥሮናል። እውነት ምን ጊዜም እንደ ጉልጭማ ፍም እሳት ነች። የፈለገ ብታዳፍኗት እሳትነቷ እንደማይጠፋ ሁሉ እውነትም የፈለግነውን ያህል ብናዳፍናት አንድ ቀን ትወጣለች ግብረ መልሷም የከፋ ይሆናል። ስለዚህ አሁን ኤንደ እናትም በእድሜ እንደገፋ ሰውም የምመክራችሁ እስከዚህ እድሜያችሁ ድረስ ያሻችሁን ስታደርጉ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን በተቻላችሁ መጠን ክፉ ላለመሆን ሞክሩ። ካልሆነ እንደ እኔ በደለኞች ሆናችሁ የሰይጣን መጫዎቻ ሆናችሁ ትኖራላችሁ። እዩ ውስጡ ንፁህ የሆነውን ልጅ እጣ ፈንታ ተመልከቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ። እኔና እናንተ ግን ያለንበትን አልነግራችሁም። በውል ጥሩ ምርት ከማያስገኝ አፈር ተቀምጠን አፈር እያነሳን ነው። ኑሯችን ሳይሻሻል እዛው ከአፈር ወደ አፈር ሆኗል። ልጆቼ አሁን የምናገራችሁ ነገር ምን አልባት አሁን አይገባችሁ ይሆናል። ምክንያቱም ገና ያልበረደ ወጣትነት ውስጣችሁ ላይ ነገር ግይ እናት ናችሁና ዘግይታችሁም ቢሆን ትረዱኛላችሁ። ግን ሲገባችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ምክር ስትፈልጉ እኔን አታገኙኝም። ገመዜ ሳይቀድማችሁ ቅደሙት እያልኳችሁ ነው ስስቶቼ"አለች የአይኗ ጭራ ላይ የደረሰውን እምባዋን ወደ ውስጧ እየሳበች። ሁላቸውም የንዝ ቃል የሚሰሙ እስኪመስላቸው ድረስ የእናታቸውን ንግግር ሳያቋርጡ በጥሞና አዳመጧት።
"እሺ እታተዬ አታስቢ በሚገባ ተረድተንሻል ነገር ግን አሁን ያልገባኝ ነገር ለምንድነው እንደዚህ በድንገት እንደዚህ አይነት ንግግር የምትናገሪው?"አለች አድና። ወይዘሮ አትጠገብ የጣራውን ቡጥር እየተመለከተች "ጥሩ ጠይቀሻል ልጄ። እንዲህ የምላችሁ ከዚህ በኋላ ለወንድማችሁ የነበራችሁን አመለካከት መቀየር አለባችሁ። ከዚህ በኋላ ለእሱ መጥፎ መሆን የለባችሁም። እንደውም በተቃራኒው ይቅርታ ብትጠይቁትና እሱም ይቅር ብኋችሁ ትንሾ ጊዜም ቢሆን የወንድምና የእህት ጊዜ ብታሳልፉ ብዬ ነው። በጣም ይጠቅማችኋል። ደግሞ ደግ ነው በእርግጠኝነት ይቅር ይላችኋል። ይቅር የማይል የእግዚአብሔር ሰው አይደለም።እስኪ ተመልከቱት ሙሉቀንን እንኳ ቀዳማዊ ከመጣ በኋላ ነው ኑሯቸው የተለወጠው። ያቺ የማትረባ እናቱ እንኳ በእኔ ልጅ እርዳታ የገዛላትን ቀሚስ ለብስ ቤተርኪያን ላይ ስታገኘኝ እንዴት እንድት እንደምትሆንብኝ። ሙሉቀንስ በአንድ በሬ አልነበር እንዴ የሚኖረው መቀናጆ ገብቶ። አሁን ግን እንደምታዩት ማንም የሌላቸውን አይነቶች በሬዎች ገዝቶ ጥንድ ጥንድ በሬ አለው። ኧረ ምኑ ቅጡ "ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ማለፊያ አቋረጠቻትና "እና ሆን ብሎ እኛን ለማናደድ ብሎ እኮ ነው ይሄን ሁሉ ያደረገለት። እያ ደግሞ ይቅርታ ያደርግላችሀዠኋል ያልሺውን አልስማማበትም። ምክንያቱም መጥቶ ምን ምን አድርጎ እንደሄደና ምን እያሰበ እንደሆነ በደንብ እናውቃለን።በርግጥ እንደሱ የተማሪ ተንኮለኛ ላንሆን እንችላለን። ነገር ግን በጭራሽ እኛም ከእሱ የበለጥን ነን ሊሸውደን አይችልም"አለች እጇን እያወራጨች። ርብቃም "የማለፊያን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማበታለሁ። እታተይ በርግጥ አሁን ላይ በዚህ እድሜሽ ፍራቻሽን ነውና የመከርሽን ምክርሽን ሰምተነዋል ተረዴተሻልንም ግን ይቅር ተባባሉ የሚለው ሀሳብ ማዘናጊያ ነው። ቀዳማዊ ያን ሁሉ አድርገነው ረስቶት ይቅርታ ብሎን ጥሩ ወንድምና እህት እንሆናለን ብዬ አላስብም"አለች። "እኔ ግን የእታተይን ሀሳብ እደግፋለን። እየውላችሁማ በደንብ አስቡት።እታተይ እንደለትው ይቅርታ ብንጠይቀው ይቅር ሊለን ይችላል። ደግሞ ከተማ ነው ያደገው ይቅርታ ከተጠየቀ ሁሉንም ነው የሚረሳው። ነገ ጠዋት በብዙ ነገሮች መገናኘታችን አይቀርም። ልጆቻችንም ከእኛ ክፋትንና ቂምን መውረስ የለባቸውም። ለልጆቻን ይህንን መተው የለብንም። ከአሁኑ ካልቆረጥነው የችግሩ ሰንኮፍ እያደገ ይሄዳል። ደግሞም ይቅር ብለን ብንጠይቅ እኛ እንጅ ሸክማችን የሚቀል እሱ የምንም የሚለው ነገር አይኖርም"በማለት የእናቷን ሀሳብ ደገፍ ከጎኗ መሆንዋን አስመሰከረች። ኤርስበርስ ሲጨቃጨቁ ቆዩ። የነ ማለፊያ እና እርብቃ ቡድንበጭራሽ ይቅርታ አንጠይቀውም ብለው አሻፈረኝ ሲሁ። የነ አድና ቡድን ደግሞ ሁሉንም እንተወው በማለት ለሁለት ተከፈሉ። "በሉ አሁን አትጨቃጨቁብኝ። በቃ እንደፈለጋችሁ እርስ በርስ ተጣልታችሁ ደግሞ መሳቂያ እንዳትሆኑ።
"ፐ ከወለዱ አይቀር እንዲህ ነው እንጅ እነሙሉቀንን እኮ የአየር ትኬት የቆረጠላቸው ራሱ ነው። መቼም ትልቅ ሰርግ ቢሆን ነው መሬት አይንካችሁ ብሎ በአየር ያስወሰዳቸው"አለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ "ልክ ብለሀል ጃል የሙሉቀንን ኑሮ እኮ በድንገት ነው ያሻሻለለት ሀሰማይ የመጣ ነው የሚመስለው። እንደዛ ለምኗን እየተንቆሻቆሸ እንዳላረሰ አሁን ግን ተጀንኗል"አለ ንቀት ባዘለ አነጋገር። "አንተው እሱ ከተሜ ከተሜ ሸቷል ተይየይ በኋበላማ ጭራሽ ጉዳችን ፈላ። ወጉ ሁሉ አየር ነው የሚሆነው።"አለ ሌላኛው የበግ ለምዱን እያስተካከለ። "አንተው የእሱን ጉራ ተወውና ግን ጥሩ ልይ ነው ድምጡ እኮ አይሰማም። እንደ ድህነቱ አይደለም ዝቅ ብሎ ነበር የሚሰራው። ፈጣሪ ያን ቆጥሮለት ነው አቦ እንዲህ አይነት ሲሳይ የሰጠው። ችግር የለም የሰራ ሰው እንኳ ያግኝ ቁጭ ብሎ ባቱን እያጠበ የሚውል ሞላጫ አይደል። ይጥራል ይለፋል። በያ ላይ ለእኩ ክፋት የለውም ደግ ነው። እንዲህ አይነት ሰው ደግሞ ማግኘቱ ደግነቱን ይጨምርለታል እንጅ አይቀንስበት።ምክንያቱም ማግኘትንም ማጣትንም በሚገባ ያውቀዋል"በማለት የሙሉቀንን ጥሩ ማግኘት ደገፈ። "ግን አንድ ቀንም አስበኸው ታውቃለህ ቀዳማዊ እንደይህ ይሆናል ብለህ?" "ኧረ በጭራሽ ጎድ እንደው አንዱ የከተማ ሰው ዱርዬ አርጎ ወያላ ይሆናል ነው እንጅ ብዬ ያሰብኩ እንደይህ ትልቅ ሰው ይሆናል ብዬ እንኳ በህልሜም አላሰብኩት እንኳን በውኔ" "አይ የጌታ ነገር እሱ እኮ ማንሳትም መጣልም ይችልበታል። እንደዛ መከራውን አይቶ እኛ ራሱ ይቺ ሴትዮ በእውነት ይሄን ልጅ ወልዳዋለች? ብለን እስክንጠይቅ ድረስ እንዳላሰብነው ከዛ ወጥቶ ይሄን ያህል ማረግ ሲያገኝ እኛስ እኛ ነን እንደ ው እነ ወይዘሮ አትጠገብ ምን ይሉ?" ብሎ በመገረም ጠየቀ።

@amba88
@ken_leboch