Get Mystery Box with random crypto!

ተፈፀ ተፈፀመ ተፈፀመ እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ ' ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአ | ከ

ተፈፀ ተፈፀመ ተፈፀመ
እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ

" ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር
ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር”
※ ※ ※ ※ ※ ※
የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ በዕቅፍሽ እንዲጠጋ እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ በርሱ ዐማጽኚ።

እመቤታችን ሁላችንን በምልጃዋ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣ከመርገም ወደ በረከት፣ ከርኵሰት ወደ ቅድስና ትመልሰን።

እንኳን አደረሳችሁ።