Get Mystery Box with random crypto!

Hossana Gospel movement

የቴሌግራም ቻናል አርማ kalihewnetnew — Hossana Gospel movement H
የቴሌግራም ቻናል አርማ kalihewnetnew — Hossana Gospel movement
የሰርጥ አድራሻ: @kalihewnetnew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 133
የሰርጥ መግለጫ

#ሀሳብ /ጥያቄ ካልዎት
@oneonesixR
☎0916536319

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-17 09:28:07 ቀን 09/09/2014ዓ.ም

ማሳሰብያ
#ከ HGM Telegram group owner & admins.

የgroupun አጠቃቀም በተመለከተ "ለዚህ group memebers በሙሉ"

ይህ ማሳሰቢያ ከተለቀቀበት ቀን ጀምሮ የዚህ group አላማ የሚጣረሱ ፦
የጽሑፍ፣የድምጽ ፣የተንቀሳቃሽ ምስል (video) እና የምስል( photograph,graphics...ሌላም) መልዕክቶችን ማስተላለፍ የማይፈቀድ መሆኑን ልንገልጽላችሁ እንውዳለን።
በተጨማሪም ከወንጌል አማኞች አብያታ ክርስትያናት ውጭ የሆኑ የትኛውን አይነት የprogram( events,concert,confrance...etc) ያለ owner እና admins ልዩ ፍቃድ በgroupu ላይ ማጋራት የተከለከለ ነው።
በአብያታ ውስጥ ያልተካተቱ የMinitry(የግለሰብ church) የትኛውም ማስታወቂያም ይሁን መልዕክቶች በፍጹም የማናስተናግድ መሆኑን ልናሳስብ እንውዳለን።

ከgroupu አላማ ጋር የሚስማሙ መልዕክቶችን የምትለቁ እና እየለቀቃችሁም ያላችሁ ወገኖች በርቱልን በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነው።

ተባረኩ .....


የወንጌል እሳት እንደገና ከሆሳዕና...

ከሆሳዕና ወንጌል ንቅናቄ ህብረት ( HGM)
84 viewsHossana Gospel Movement EYOB, edited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 10:06:57
184 viewsHossana Gospel Movement EYOB, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:49:20 ይህን ሊንክ @kalihewnetnew
ለወዳጆቻችሁ አጋሩ
150 viewsHossana Gospel Movement EYOB, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:42:09 Channel name was changed to «Hossana Gospel movement»
18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:06:19
136 viewsHossana Gospel Movement EYOB, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 20:39:26 Channel photo updated
17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 21:15:49 @thefireofgospel join now
110 viewsHossana Gospel Movement, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:05:05 አስታዋሾች...... ፈላጊዎች


ወንድሜ በቀን ስንት ሰው ይደውልልሃል? ስንቴ ነው ስልክህ የሚጮኸው? ከዘወትር አፍቃሪህ ከቴሌ ሌላ ስንት ሰው ቴክስትስ ያደርግልሃል?

አዎ አንተ ፈላጊህ ከመብዛቱ የተነሳ ደላላ ሆንክ እንዴ? ትባላለህ ሌላኛው ደግሞ በቀን አይደለም በሳምንት እንኳ ስልኩ ጮኾ የማያውቅ "እኔን ሰው አይፈልገኝም ስለዚህ መኖር የለብኝም" በማለት ራሱን ለማጥፋት የወሰነም አለ። ይህን የምለው እንዲሁ በግምት አይደለም ደቡብ አፍሪካ ላይ የተፈጠረን ክስተት በማስታወስ ነው።

በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካ በተፈጠረው ወቅታዊ ክስተት ሰቢያ ቁጥራቸው ከ5000 በላይ በሚሆኑ ወጣቶች ላይ በተደረገ ጥናት መሰረት ተቀባይነት በማጣት ስሜት ህይወታቸው ጥያቄ ውስጥ እንደነበር በየሚድያው የውይይት ርዕስ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ምክንያቱ ከሞባይል ጋር በተያያዘ ሲሆን እነዚህ ወጣቶች በያዙት ተንቀሳቃሽ ስልክ ይደውላሉ እንጂ አይደወልላቸውም። ይህ ደግሞ አንድ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ አስገደዳቸው በቃ እኛ ተፈላጊዎች አይደለንም የሚል። በዚህ የተነሳ ብዙ የስነልቦና ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ የትኩረት አቅጣጫቸውን ወደ እነርሱ አደረጉ።

" የሰው ልጅ ሊያስተናግደው የማይችል ከባድ ነገር በሰው ዘንድ ተቀባይነት ማጣት ነው" የሚባለው ለዚህ ነው። ቃየል ወንድሙን አቤልን የመግደሉ ምክንያት በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱ ነው። ቃየል ፈገግታና ደስታ የማይለየው ሰው ነበር መሰል እግዚአብሄር "ለምን ፊትህ ጠቆረ መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አልነበረምን" ዘፍ 4፥6 ሲለው እንመለከታለን።

ወንድሙ አቤልን በመግደል ሞት ምን እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰው ልጆች ሁሉ እንደመልካም ነገር አስተዋወቀ። አይ አለመታደል ቃየል ሞትን ሲያስተዋውቀን ጌታ ደግሞ ህይወትን አስተዋወቀን፤ ቃየል በወንድም ላይ መጨከንን ሲያስተዋውቀን ጌታ ደግሞ ርህራሄን አስተዋወቀን።

ወዳጆቼ ብዙ ነገሮችን እንደቀላልና እንደተራ ነገር እንቆጥራቸው ይሆናል ከዚህ መሀል መጥፋታችን አሳስቧቸው የሚደውሉልን፣ የድምፃችን ሽታ ናፍቋቸው የሚደውሉ፣ እኛን ሲያወሩ የሚደሰቱ ሲደውሉልን "ደግሞ ደወለ" ብለን ደቂቃ ለመስጠት እንወጠራለን። እኛ እንደ ተራ እንየው እንጂ እግዚአብሄርን የምናመሰግንበት ርዕሳችን መሆን ነበረበት።

ብዙ ድምፅ የራባቸው ባዶ ጆሮዎች ባሉበት የኛ ጆሮ የወዳጅን ድምፅ መስማቱ መታደል ነው። እኛም ሰው ሆነን ናፈከኝ ተብለን ሲደወልልን መታደል ነው። ዛሬ ስለኛ ተጨንቀው ጠፋችሁ ብለው የሚደውሉልን ወዳጆች ካሉን በሰው ልብ እንድንታሰብ ያደረገን እግዚአብሄር ይመስገን።

ጠፋህ ብላችሁ ስለምትደውሉልኝ፣ በልባችሁ ስለምታስቡኝ፣ እንደ ወላጅ መውጣት መግባቴ ጨንቋችሁ ለምትደውሉልኝ ሁሉ ክብረት ይስጥልኝ እግዚአብሄር በልቡ መዝገብ ይፃፍልኝ ተባረኩልኝ።


#በወንጌል_አላፍርም
177 views@በወንጌል~አላፍርም, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:05:04 አንቺ ለኔ .....እኔም ላንተ

   
      ሕይወት ውሏ ጠፍቶብሽ መኖሬ ማንን ይጠቅማል? አለመኖሬስ ማንን ይጎዳል? እያልሽ ከራስሽ ጋር ተናንቀሽ ይሆን? አይዞሽ እህቴ ታስፈልጊያለሽ። አንቺ ለዚህች ምድር ለውጥ ፈጣሪ ባለ ብዙ አቅም ብርቱ ሴት ነሽ። እግዚአብሄር የፈጠረኝን ቦታ ብቻ ሸፍኜ ልኑር አትበይ። አንቺ የምታኖሪው ብዙ ነፍስ አለ። ያለ አንቺ የማይሞላ፣ ያለ አንቺ ጎዶሎ የሆነ፣ ያለ አንቺ የማይደምቅ ብዙ ነገር አለ። ዛፍ የተተከለበትን ቦታ ብቻ ሸፍኖ አይኖርም እኛንም ያኖራል። አንቺም ለብዙ ተርፊያለህሽ። ዛፍ የተቃጠለውን አየር ውጦ ኦክስጅን የሚተነፍሰው ለኛ ነው። ያለማቋረጥ ህይወት ይሰጠናል። አንድም ቀን ተሳስቶ ሞትን ሰቶን አያውቅም ሁሌም ህይወትን ይተነፍስልናል።

   ታውቃለህ ወንድሜ? አሁን ከመንገድህ ባገኘኸው ታክሲ ብትገባና ታክሲ ሰው ጭኖ ሞልቶ ሊሄድ ሲል ወራጅ ብለህ ከታክሲው ብትውርድ የሞላው ታክሲ ይጎላል። ታክሲው አይሄድም ረዳቱ መጥራቱን ይቀጥላል፤ አንድ ሰው የሞላ ይላል፤ አንተ ያጎደልከውን ቁጥር ሊሞላ ቆሞ ሌላ ሰው ይጠብቃል።

    እንዲህ አድርገህ አስበው! አንተ ከታክሲው በመውረድህ ታክሲው ሌላ ሰው ለመጫን ሶስት ደቂቃ ቢቆም ረዳቱንና ሹፌሩን ጨምሮ በአስራ ሶስት ሰው ህይዎት ላይ የሶስት ደቂቃ ልዩነት ፈጥረሃል ማለት ነው። አስበው አንተ ብቻህን የአስራ ሶስት ሰው ህይዎት ላይ ሶስት ደቂቃ ታጎላለህ። በተቃራኒው አስበው አስራ አንድ ሰው ጭኖ አንድ ሰው የሞላ ለሚል ታክሲ ሮጠህ ብትገባ ሞልቶ ቢሄድ ለነዚያ ለአስራ አንዱ ተሳፋሪዎች የሆነ ደቂቃ በህይዎታቸው አትርፈሃል።

    ይሄ ነው የአንተም የአንቺም በህይዎት የመኖር አስፈላጊነት! የኔ በህይዎት መኖር ለማንም አይጠቅምም አትበሉ። ካላጎረስክ፣ ካላለበስክ፣ ገንዘብ ካልሰጠህ መኖርህን የምትረሳ ከሆነ የእውነት መኖርህን ዘንግተሀል ወዳጄ ምክንያቱም ካላጎረስከው የማይጠግብ፣ ካልሰጠኸው የማያገኝ ብዙ አለ። ህይወት መዋቅሯ እርስ በእርስ የተገመደ ነው። እጄን ያዘኝ እጅህን ልያዝህ ታስፈልገኛለህ እኔም አስፈልግሃለው።

     ወዳጆቼ ለሰው ቀርቶ ለእግዚአብሔር ታስፈልጉታላችሁ። ባንተ ምስክርነት በአንተ ስብከት የእግዚአብሔር መንግስት ይሰፋል። እግዚአብሔር በአንተ ብቻ የሚሰራው ስራ አለው። እግዚአብሔር በአንቺ ብቻ የሚሰራው ስራ አለው። አለምልጠቅምም አትበይ ካንቺ በላይ ጠቃሚ ማን ነው ከአንተ በላይ ጠቃሚ ሰው ማን ነው? በርቱና በተስፋ ኑሩ!


#በወንጌል_አላፍርም
108 views@በወንጌል~አላፍርም, 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ