Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊጉባኤ አባላት በሙሉ ልበ አምላክ ዳዊት “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳውም | "ቃለ እግዚአብሔር "

መንፈሳዊጉባኤ አባላት በሙሉ ልበ አምላክ ዳዊት “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳውም ጠልን ይጠግባል” (መዝ.፷፬.፲፩) በማለት እንደ ዘመረው ቸርነቱ ወሰን የሌለው አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን በሰላምና በጤና አሸጋገረን። እጅ ለእጅ ተያይዘን በመተባበር ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ለመፈጸም ራሳችንን የምናዘጋጅበት፣ በአንድ አሳብ አቅደን በመሥራት፣ “ዘመኑን ዋጁ” ተብሎ የተነገረንን በተግባር ለመፈጸም የምንዘጋጅበት ዘመን ያድርግልን


"የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኃጢኣት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምወዳችሁ መንፈሳዊ እህትና ወንድሞቼ በቸርነቱ ስላደረሰን አዲሱ አመት በማስቀደስ አምላካችንን ምስጋና እናቅርብ
እህት ውንድሞቼ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በውስጥ መስመር እንኳን አደረሰን እንባባል ውስጥን ያድሳል
አዲሱ አመት አምላክ የውስጣችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ ከልቤ እውዳችኃለው



መልካም አዲስ አመተ