Get Mystery Box with random crypto!

ስኬት ስኬት ስለሚለው ቃል ስናስብ መቼም ሁላችንም ልብ ውስጥ የሚመጡ ይሄን ይሄን ባሳካ ብለን በ | "ቃለ እግዚአብሔር "

ስኬት

ስኬት ስለሚለው ቃል ስናስብ መቼም ሁላችንም ልብ ውስጥ የሚመጡ ይሄን ይሄን ባሳካ ብለን በልባችን ውስጥ የምናስባቸው፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስኬቶች ይኖሩናል። ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ በአካባቢያችን ላይ የምናውቃቸው ወይንም በsocial media ገጾቻችን እነሱ እንኳን ሳያውቁን እኛ የምናውቃቸውና የምንከተላቸው፣ በየቀኑ የሚያወጡትን ፎቶዎች እያየን የስኬት ምሳሌዎች ያረግናቸው ሰዎችም ይኖራሉ። ስኬት ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም ያለውና በህይወት ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች ጋር የተያያዘ ነገር ነው። ለአንዳንዱ በልፋቱ የሚያገኘው ደሞዝና ዋጋው ነው። ለሌላው ደግሞ ትምህርቱን ጨርሶ ያሰበውን ስራ መያዝ ማግባትና መውለድ ሊሆን ይችላል። ለሌላው ደግሞ አካባቢው ባሉ ሰዎች ወይንም በብዙሀኑ ዘንድ በሰራው ስራ እውቅናና ዝናን ማግኘት ሊሆን ይችላል። “ለእኔ በጤናና በሰላም ስራዬን ሰርቼ የቀን ለቀን ውሎዬን በሰላም ካለፍኩ ስኬት ነው” የሚሉ ሰዎችም አሉ። እነዚህ ሁሉ ከላይ የዘረዘርናቸው ነገሮች ምንም ክፋት የሌለባቸው፣ እንዲያውም በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ሊያስፈልጉን የሚችሉና የምንጠቀምባቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ደግሞ ልክ እንደ አንድ ክርስቶስን በህይወቱ አምኖ ለመኖር እንደወሰነ ሰው ሆነን ህይወትን ስናየው ከሌሎች ክርስቶስን ከማያምኑ ሰዎች ለየት ያለ የስኬት ትርጉም ሊኖረን እንደሚገባ እናስተውላለን። ለመማር፣ ለማግባትና ለመውለድ የክርስቶስን አማኞች መሆን አይጠበቅብንም። እንዲያውም፣ ስኬትን በእነዚህ ነገሮች ከተረጎምነው፣ ከእኛ በላይ በብዙ እጥፍ የተሳካላቸው ብዙ በጌታችን ኢየሱስ በክርስቶስ የማያምኑ ሰዎች በምድራችን ላይ አሉ። ታዲያ ከተጠራንበትና ነገሮችን በሙሉ ልንመዝንበት ከተሰጠን ህይወት አንጻር ስኬትን እንዴት እናየዋለን?

እኛ ስኬትን ለየት ባለ መንገድ እንድናየው የሚረዳን የውስጥ አይኖቻችን ተከፍተው ከዚህች አጭር 70 እና 80 አመት ቀጥሎ የሚጀምር ዘላለም የሚባል ቁጥር የማይወስነው ዘላለማዊ የሆነ ህይወት እንዳለ መረዳታችን ነው። አያችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የማያምኑ ሰዎች ስኬትን የሚተረጉሙት አይናቸው ሊያይ እስከሚችለው 70 እና 80 አመት ርቀት ብቻ ነው። ህይወታቸውን የሚያቅዱት በዚህች ምድር ቆይታ ላይ ብቻ ተመስርተው ነው። ስለዚህ ስኬት ለእነሱ አብዛኛውን ጊዜ የተያያዘው፣ ከዚህች ምድር ምቾት ጋር ብቻ ነው። እኛ ግን ስኬትን የምናየው፣ ከዚህች በጣም አጭር የምድር ቆይታ አልፈን እንድናይ እግዚአብሔር በሰጠን ሰፊ እይታ ውስጥ ሆነን ነው። ስለዚህ በጣም የምንጨነቀው ለዚህች ምድር አጭር ቆይታችን አይደለም። ለዘላለም ነው። የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እያነበብን ስንመጣ፣ በቃሉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሐሳብ እና ፈቃድ እየተረዳነው እንመጣለን። ሀሳቡን እያወቅነው፣ ከሚናገራቸው ንግግሮች፣ ከሚሰጣቸው ምሳሌዎች፣ ደጋግሞ ትኩረት ከሚሰጥባቸው ሀሳቦች፥ ዋጋ የሚሰጠው ምን ላይ እንደሆነ፣ የሚያተኩረው ምን ላይ እንደሆነ፣ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እየተረዳን ወይንም እያወቅነው እንመጣለን። ታዲያ እስከዛሬ ድረስ ካነበብነው ወይንም በስብከትና በትምህርት ከሰማነው አስተውለን ካየነው፥ እግዚአብሔር ከምንም ነገር በላይ፥ ትኩረት ወይንም ቅድሚያ የሚሰጠው ዘላለም ለሚባለውና ይህቺን አጭር የምድር ቆይታ ስንጨርስ ስለምንጀምረው ህይወት ነው። እግዚአብሔር ስሙ ወይንም መጠሪያው የዘላለም አምላክ፣ መንግስቱና ዙፋኑ የዘላለም፣ ምህረትና ፍቅሩ የዘላለም፣ ለእኛ የሰጠንም ህይወት የዘላለም ነው። ወንጌል በጣም አስፈላጊና የእግዚአብሔርን ልብ የያዘ ነገር የሆነው የሰዎችን የዘላለም አድራሻ ወይንም የዘላለም መኖሪያ የሚቀይር ነገር ስለሆነ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር የልቡ ትርታ ዘላለም ከሚለው ቃል ጋር በጣም የተሳሰረ ነው። ይሄ አሁን እየተነጋገርንበት ያለነውን ነገር የሚያጠናክርልንንና በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 18 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተናገራቸው ነገሮች ውስጥ እስኪ አንዱን እንመልከት። አንድ ጊዜ ስለ ማመንዘር ትምህርት ሲሰጣቸው እንዲህ አለ። ቀኝ አይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት ሙሉ ሰውነትህ በገሀነም ከሚጣል፣ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሀልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፣ ሙሉ ሰውነትህ በገሀነም ከሚጣል ይልቅ፥ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና አላቸው። አያችሁት ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እይታ ብዙ ጊዜ እኛ ስንቀልድ እንኳን፥ በአይኔና በዚህ ሰው ቀልድ አላውቅም እያልን እንናገራለን። እውነት ነው አይን በጣም አስፈላጊ ከምንላቸው የሰውነት ክፍሎቻችን አንዱ ስለሆነ ነው። እንደ ጌታችን ንግግር ከሆነ ግን፥ በጣም አስፈላጊ ነው ከምንለው ከአይናችን በላይ ሌላ በጣም አስፈላጊ ነገር አለ። እሱም ደግሞ ዘላለማችንን የምናሳልፍበት ቦታ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ በሆነ እይታ ውስጥ ሆኖ ሲያየው፣ በምድር ላይ አስፈላጊ የምንለውን ነገር አጥን ዘላለማችንን ከእርሱ ጋር ብናሳልፍ ነው ያተረፍነው። በምድር ላይ አስፈላጊ የምንለው ነገር ዘላለማችንን ካሳጣን የጌታችን ፍርድ ይሄ ነው አውጥታችሁ ጣሉት ወይንም ቆርጣችሁ ጣሉት። በጣም ይጠቅመኛል ብለን የያዝነው ነገር፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት ካበላሸብን፣ አውጥተን ጥለነው እግዚአብሔርን ወይንም ዘላለማችንን በጥንቃቄ ብንጠብቀው ትልቅ ማስተዋል ነው። ከአይናችን በላይ ልንጠብቀውና ልንንከባከበው የሚገባን ነገር ቢኖር፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ልጅነት እና ዘላለማችንን ነው።

እግዚአብሔር ዘላለም ለሚባለው ህይወታችን የሚሰጠውን ቦታ በድርጊት ወይንም በስራ ካየንባቸው ነገሮች ዋነኛው፣ የእኛን የዘላለም አድራሻ ይቀይር ዘንድ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር መላኩ ነው። መዳናችን፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ በማመን ብቻ ያገኘነው ስጦታ እንደሆነ እናውቃለን። ሁልጊዜ መርሳት የሌለብን ግን፣ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ እንጂ፣ ጌታችንን ግን ያላስከፈለው ዋጋ አልነበረም። ነጻ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ ነው። ጌታችን ግን እያንዳንዱን የውርደት ጥግ ያየባቸው አሰቃቂ 33 አመታቶች ናቸው። እኛ ሰዎች ስለሆንን ለእኛ ሰው መሆን ቀላል ነው። መጽሐፉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነግረን ግን በሰው ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፣ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ይለናል። መድኃኒዓለም ራሱን ማዋረድ የጀመረው፥ የሚሰቀልበት ሰአት ሲደርስ አይደለም። መስቀል ላይ ሲውል አይደለም። ራሱ ከምድር አፈር የሰራውን ሰው ለመሆን ሲወስን ነው። ራሱን ሰው ለማድረግ ከመወሰኑ አንስቶ፣ በምድር ላይ አለ በተባለው ውርደት ስቃይና መከራ ውስጥ የማለፉ ምስጢር፥ እግዚአብሔር ዘላለም ለሚባለው ህይወት ያለውን ቦታ በትክክል ሊያስረዳን ይችላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እያለ የተለያዩ ሰዎችን በመፈወስ፣ ከሰይጣን እስራት ነጻ በማውጣትና በተለያዩ መንገዶች የሰው ልጆችን የረዳ ቢሆንም ዋናው የመጣበት አላማ ግን የእኛን ዘላለም ለማስተካከል ነው። እንዲያውም በምድር ላይ የሰራቸው እያንዳንዱ ተአምራቶች ወደ ምድር የመጣበትን የዘላለም ህይወት ጉዳይ ሰዎች እንዲሰሙና እንዲረዱ ልባቸውን ለማግኘት የተጠቀመባቸው መንገዶቹ ነበሩ። ከጌታችን በሁዋላ የሐዋርያትንም አገልግሎት ስታዩ፣ በሐዋርያቱ እጅ እጅግ ብዙ ድንቅና ተአምራቶች ይደረጉ ነበር። የሚገርማችሁ ግን፥ የትኛውንም ተአምራት ስታነቡ፣ ከእያንዳንዱ ተአምራት በኋላ፥