Get Mystery Box with random crypto!

​(መልክአ ትህትና) ሰላም ለውብ ስምሽ ቃናው ለሚጣፍጥ አፈ መዓር አንቲ ለጆሮ የሚመስጥ መሠረተ | "ቃለ እግዚአብሔር "

​(መልክአ ትህትና)

ሰላም ለውብ ስምሽ ቃናው ለሚጣፍጥ
አፈ መዓር አንቲ ለጆሮ የሚመስጥ
መሠረተ ህይወት የቅንነት መዝገብ
እመ ትህትና የ'ሲሎንዲስ ጥበብ

ሰላም ለጉሮሮሽ ጥዑም ቃል ለሚያፈስስ
አንደበትሽ ትሁት ቁጣን የሚመልስ
በቃልሽ ሰምተሽው በልብሽ የጠበቅሽ
የአርምሞ ገዳም የፀጥታ አዳራሽ

ሰላም ለእጆችሽ አምላክ ለታቀፉ
በረጃጅም ጣቶች እውነትን ለጻፉ
የህይወት እንጀራን በእጆችሽ አቅፈሽው
ህብስት ይዘሽ ሳለ ቁራሽ የለመንሽው
ትህትናሽ ይደንቃል!

ሰላም ለእግሮችሽ በእሾህ ላጌጡ
ከፍታነት ንቀው ታህት ለረገጡ
ኀበ ቤተመቅደስ ገስግሰው ለሮጡ
ሀሩር ቁሩን ችለው ስደት ለመረጡ
መከራው ቢፀና ድካም ቢበረታ
አላጉረመረመች ከአፏ ቃል ስታ
ይህች ዕፀ ህይወት
በእውነት ትሁት ናት!

ሰማያዊት መዝገብ የትሁታን ራስ
ምክኾን ደናግል የሲና ዕፀጳጦስ
የደስታ መገኛ ሀገረ ክርስቶስ
ምን ቃላት ሊገልፀው ያንቺን ትህትና
የምድር መካከል ርኅርኅተ ህሊና
እሙ ለአዶናይ ድንግል ሶልያና

ትህትና ቃሉ ትርጉም አያሻውም
ውበቷም ትሁት ነው ቃላት አይረባውም
ድንግል ናት ትህትና ትህትናም ድንግል
ተስፋሁ ለአዳም የድኅነታችን ቃል!

ዮሐንስ ዓይናለም

@kaleEgziabeher