Get Mystery Box with random crypto!

#ሊነበብ_የሚገባ_በጣም_መሳጭ_እና_አስተማሪ_ታሪክ ውፍረቷ ያስጎመጃል፣በጣም ተስማምቷታል ጋቷ በ | 𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

#ሊነበብ_የሚገባ_በጣም_መሳጭ_እና_አስተማሪ_ታሪክ
ውፍረቷ ያስጎመጃል፣በጣም ተስማምቷታል ጋቷ በወተት ተሞልቶ ሊፈነዳ ተቃርቧል ይቺን ግመል ሰደቃ ለማድረግ ወሰንኩ

ይህ ልጆቹ አባታችን ሞቷል ብለው በህይወት አያለ ንብረቱን የተከፋፈሉት የኢብኑ ጁድዓን አስደናቂ ታሪክ ነዉ

አላህ "የምትወዱትን አስካልለገሳቹ ድረስ የበጎ ስራን ዋጋ አታገኙም ብሏል ስለዚህ አኔም ምወዳትን ግመሌን መለገስ አለብኝ ብሎ ለድሀ ጎረቤቱ መፀወተ

ድሀው ሰው ደስታውን መግለፅ አቃተው ስሜቱ በፊቱ ላይ ይነበባል እንዲህ አይነት ትልቅ ነገር ቤቱ ሲመጣ ደስታውን መቆጣጠር አልቻለም

ፀደይ አልፎ በበጋ ተተካ በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ ኢብን ጁድዓንን ከልጆቹ ጋር ውሃ ፍለጋ እንዲወጣ አስገደደው ሶስቱ ልጆቹን እንዲጠበቁት በማድረግ ወደ ምድር በሚያስገባ ጉድጓድ ገባ ለመጠጥ የሚሆን ውሃ ለማውጣት አስቦ ነበር ዳሩ ግን ኢብን ጁድዓን የገባበት ጉድጓድ ጥልቅ በመሆኑ ተሰወረ 1ቀን 2ቀን 3ቀን አለፈ
ልጆቹ -አለህ ይጠብቀንና-የአባታቸውን ንብረት ለመውረስ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ የአባታቸውን ሞት ይጠባበቁ ነበር ወደቤት በመሄድ ንብረቱን ተከፋፈሉ በመሀል አባታቸው ለጎረቤት የሰጠውን ግመል አስታወሱ ወደ ሰውየው በማምራት ለሰውየው ግመሏን መልስ በምትኳ ሌላ እንሰጥሃለን እንቢ ካልክ በባዶ እንወስድብሀለን አሉት ሰውየውም ይህንን ስራቹን ለአባታቹ እናገራለሁ በማለት አስፈራራቸው -"ሂድ ንገረው እሱ ሞቷል አሉት ሞተ! መቼ ሞተ ! እኔ መች አወቅኩ "በማለት አዘነ
የከርሰ ምድር ውሃ ፍለጋ ጉድጓድ ገብቶ ሞተ አሉት እባካችሁ የሞተበትን ቦታ አሳዩኝ ከፈለጋችሁ ግመሉን ውሰዱ ቅያሪም አልሻም አለ
ልጆቹ ጉድጓዱን አሳይተው ግመሉን ተቀበሉ
ሰውየው ወደ ጉድጓዱ ሻማ እና ገመድ ይዞ ገባ ገመዱን ከላይ ባለ ቋጥኝ አስሮ ነበር ወደ ውስጥ የገባው አየዳበሰ ፍለጋውን ቀጠለ በመጨረሻም እጁ ከኢብኑ ጁድዐን ሰውነት ላይ አረፈ ሳምንት ቢቆይም ትንፋሹ ይሰማል በፀሀይ ብርሀን እንዳይጎዳ አይኑን በጨርቅ ሸፎኖ አወጣው መገበው ፣አጠጣው አዝሎም ወደ ቤቱ ወሰደውይህ ሰው በድጋሚ ህይወት ዘራ ልጆቹየሆነውን አላወቁም ነበር አንዴት አንድ ሳምንት በዚህ ሁኔታ ቆይተህ
አልሞትክም ብሎ ጠየቀው

ወደ ጉድጓዱ ስገባ መሬቱ ተደረመሰ ወደታች ይዞኝ ገባ በቦታው ውሃ ስለነበር ውሀ ጠጣሁ ግን ምግብ አላገኘሁም ያለምግብ መቆየት ደግሞ ይከብዳል ረሀቡ በረታብኝ ተንጋልዬ ተኛው ነገሬንም ለአላህ ስጠሁ በዚ መሀል ከአፌ ለይ ወተት ይንደቀደቅ ጀመር ተስተካክዬ ተቀመጥኩ የወተት እቃ ወደ አፌ ሲቀርብ ይሰማኛል ግን አይታየኝም አስክጠግብ እጠጣለሁ ከዚያም ከኔ ይሄዳል በቀን ሶስቴ ይመጣልኛል ግን ከ2ቀን በፊት ተቋርጧል" አለ ጎረቤቱም "ልጆችህ የሞትክ መስሎዋቸው አላህ ከወተቷ ያጠጣህ የነበረችውን ለኔ የለገስከኝን ግመል ወሰዷት ለዚህ ነው የተቋረጠው አለው ።
ሙስሊም ምን ግዜም በሰደቃው ጥላ ስር ነው