Get Mystery Box with random crypto!

I Think የዓለም ፍፃሜ ደርሶ፣ ዓለም ሊጠፋ ሆኖ የእሳት-ዝናብ-ከሰማይ ወደ ምድር ቢወርድ እና | 𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤



I Think የዓለም ፍፃሜ ደርሶ፣ ዓለም ሊጠፋ ሆኖ የእሳት-ዝናብ-ከሰማይ ወደ ምድር ቢወርድ እና ሰዎች ሊያልቁ ቢቃረቡም እንኳን የአብዛኛው የሰው ልጅ የመጨረሻ ቃላት የሚሆነው “ደህና ነኝ” ይመስለኛል።

ሰዎች አንዳንድ ጊዜ አሰቃቂ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው አይቻለሁ። አብዛኛው ሰዎች የሚወዱት ሰው ቢሞትባቸው ፣ ፈተና ቢወድቁ ፣ በGrade ቢወድቁ ፣ከትዳር አጋራቸው ጋር ቢፋቱ ፣ ከስራ ቢባረሩ፣ ቢጎሳቆሉ ፣ ደባሪ እና አሰልቺ ቀን ቢያሳልፉም የአብዛኛዎቹ መልስ ሊሆን የሚችለው “I’m fine.” “ደህና ነኝ " ነው።ይኼ ወንዶችም፣ ሴቶችም፣ አዋቂዎችም፣ተማሪዎችም፣ ሁሉም ሰዎች የምናደርገው ነው፡፡

እኛ ምናስበው ወንዶች ጠንካራ እና ቆፍጣና መሆን ስላለባቸው ሁሌም “ደህና” እንደሆኑ ነው ፣ እናም በሆነ ነገር አዝነው መታየት ልክ እንደ ደካማነት ነው ሚታይባቸው፣ So የእነሱ እርዳታ መጠየቅ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም ስለዚህ ደህና እንደሆኑ ያስመስላሉ።

እኛ ምናስበው ሴቶች ሁሌም “ደህና” መሆን አለባቸው ብለን ነው፤ ምክንያቱም መበሳጨት ወይም ማዘን ልክ እንደ ማራኪ ያልሆነ እና ፊታቸው ላይ አስከፊ ገፅታ ይታይባቸዋል ብለን ስለሆነ ደህና እንደሆንን ለማሳየት ሁሌም Fake smile እንፈግጋለን። አንዳንዴ ለሌላ ሰው ህመም ምን ምላሽ መስጠት እንዳለብን አናውቅም፡፡ የእነሱን ሕመም እኛ እናቀለዋለን እናም ከችግራቸው ይበልጥ የእኛ መልስ ተስፋ ያስቆርጣቸዋል። ለዛ ሁሉም ሰው ማስመሰልን ይመርጣል።

So በማንኛውም ምክንያት ደህና ካልሆናቹ፣ its okay በማንኛውም ምክንያት የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማቹ ወይም እራሳቹን አትውቀሱ! You’re not annoying! ሁሉም ነገር በዚህ ያልፋል፣ነገአችንም ከዚህ የተሻለ ይሆናል! በአጠቃላይ I love to tell you that you’re loved and you’re important!
እና ደግሞ It’s Okay To Not Be Ok!