Get Mystery Box with random crypto!

#ልዑል_ወልደ-#አብ( ግጥም በታሜ(ሳሚ) ነፍስ ከማወቁ እስከ ሽምግልና የብራናው ጥቅልል ብሉዩ | የአዲስ ኪዳን ካህናት

#ልዑል_ወልደ-#አብ( ግጥም በታሜ(ሳሚ)

ነፍስ ከማወቁ እስከ ሽምግልና
የብራናው ጥቅልል ብሉዩ ሲጠና
'ምንድን ይሆን መላው?' ያረጀን ለት ጉድ ነው
አይናችን ሲደክም ማንበቡ ሲሳነው
ሲሉ የተጨነቁ
ለአይናቸው ጤንነት የተጠነቀቁ
እኚያ ሊቃውንቱ
ዕውቀት ፍልስፍናን የመረመሩቱ

መፃህፍት ወደ ልጁ ሲቀስቱ እንዳሉ
ሚስጥረ ሰማይን ባያውቁት በውሉ
በትንቢቱ ተስፋ ና'ፍቀውት ናፍቀውት
'መጣሁላችሁ' ሲል ጀርባቸውን ሰጡት

እንደምን መክሰር ነው ከከፍታ መውደቅ
ሲወጡበት ከርመው ከስኬቱ ማማ መሰላሉን መልቀቅ
ሲጓዙ መፀለይ ሲቀመጡ ማንበብ
በታወረ ፈረስ በሽምደዳ ጋሪ በፍጥነት መጋለብ
መድረሻው አያምር ግጥሙም ቤት አይመታ
ከጥንቱ ጀምሮ የሰሙት ያ ጌታ

ሁሉን በወረሰው በዓለማት ፈጣሪ
በክብሩ ነፀብራቅ አምሳለ ባህሪ
በስልጣኑ ቃላት ሁሉን በደገፈው
ያለ አንዳች ምሰሶ ሰማይን ባፀናው
ተራራ ሳንወጣ ደመና ሳይከበን
በመለኮት ሙላት ራሱን ሊገልጥልን
በልጁ ሲናገር ልባችን ካልሰማ
ከዚህ የተሻለ መናገሪያ መንገድ አብም የለውማ

ስሙኝ ልንገራችሁ
ልዑሉ ከመላዕክት አብዝቶ ይበልጣል
ከእነርሱ መሀከል ከቶ የትኛውን 'ልጄ ነህ' ብሎታል??
እሱን ተውትና
የትኛውን መልዓክ በአብ ቀኝ አያችሁ?
በልባችሁ መቅደስ በክርስቶስ ዙፋን ሌላ ያኖራችሁ
በእግዜር መልክ ቀርቶ በስጋ ሲገለጥ
ወድቀው እንዲሰግዱ እንደታዘዙለት
ማን በነገራችሁ

አይናችሁን አንሱ ከነቢያቱም ላይ
ጌታ መድሃኒያለም መልክተኛ ሳይሆን : ነው መልዕክተ ሰማይ
ነቢያቱማኮ
ምስክሮች ሆነው ልክ እንደ ደመና
ዝናብ እንዲመጣ ሰብከውናልና
እነሆኝ ኢየሱስ: የህይወት ምንጭ ውሃ
በፍቅሩ የሚያርስ የልብን በርሃ
ነቢያቱ በእርግጥ
'ከሀጥያት ተመለሱ ንስሃ ግቡ'አሉን
እርሱ ግን በደሙ
በራሱ አነፃው ሀጥያታችንን

ይሄ ጌታ ኢየሱስ
ከምትመኩበት ከሙሴም ይበልጣል
ይገደል ብትሉም ይሰቀል ብትሉም
ለራሱ ለሙሴ
'ያለና የሚኖር' እኔ ነኝ ብሎታል

እርሱ መድሃኒያለም ባሸነፈው ምድር
በመከራ ብዛት ልባችሁ ሲሸበር
"አዝናለሁ ጌታዬ: አንተ እስከምትመጣ ሁሉ ደና ነበር "
በሚለው በሚለው
ክርስቶስን ቀምሶ ወደ ሙሴ ጉዞ
ቅንጣትን መናፈቅ እልፍ አእላፉን ይዞ
ውድቀት ነው ሚዛኑ አይበጅም ስለ እውነት

ላመኑበት ሁሉ የመዳን ማህተም የሆነው ያ ትሁት
ለሚብሰው ቅጣት የኩነኔ አንቀፅ ነው ከዓለም ላሳነሱት
ብቻ ብቻ
ያ'ላጋን እንደሆን ፈተናው መዓቱ
መሰበር ማዘኑ መውደቅ መነሳቱ
ዘንግተነው እንጂ አንድ ነው እውነቱ

ከሀጥያት በስተቀር ተፈትናልና
ህመማችን በእርግጥ የሚያመው ነውና
"አንተ ምን አለብህ?' ላንለው በድፍረት
ቀድሞ ሄዷልና በምንሄድበት
የሰማይ ጠበቃ ለላቀው ክህነት
ደግሞም የታመነ የሚራራ ረዳት

መሆኑን በማወቅ
አይናችንን መትከል በልጁ ብቻ ላይ
የሚያበቃን ፀጋ ለመንግስተ-ሰማይ
ይቸረናልና
ከቶ አንሸቅጠውም የእርሱን ልዕልና !!

የዕብራውያን መልዕክት : ልጥፉን Share እወዳችኋለሁ

@untothelamb
@untothelamb