Get Mystery Box with random crypto!

#ጅማ #የኤፌሶን_መልዕክት_ጥናት #እኔ_ማነኝ?? (በህመም አይሳቅም: እንዳትስቁ) አንድ ጊዜ Ps | የአዲስ ኪዳን ካህናት

#ጅማ #የኤፌሶን_መልዕክት_ጥናት #እኔ_ማነኝ??

(በህመም አይሳቅም: እንዳትስቁ) አንድ ጊዜ Psychiatric disorder(የአዕምሮ ህመም) ያለበት ታማሚ ለብዙ ጊዜ ከህመሙ የተነሳ #ባቄላ_ነኝ ብሎ ያምን ስለነበር ዶሮ ባየ ቁጥር እየፈራ ይሸሽ ነበር። እናም ከብዙ የስነ-አዕምሮ ህክምና treatment በኋላ ሰው መሆኑን አስረዱት። ከዚያም ከስንት ትግል በኋላ ምን ቢል መጥፎ ነው?? "እሺ አሁን ለእኔ ሰው መሆኔን አስረዳችሁኝ ግን ለዶሮዋ ማን ይነግራታል? " ነበር ያለው። አያችሁ ሰው #እንዲህ_ነኝ ብሎ ያመነውን ነገር በቀላሉ ማስጣል አይቻልም።ሰውም ሀጥያት የሚባል በሽታ ካመጣበት Psychic disorder ምክንያት በክርስቶስ ፀድቀሀል እየተባለ ይሄን እውነት ሲፈራና #ሲሸሽ ይኖራል።(ማንነቱን ባለመረዳቱም ለተሸነፈው ሰይጣን ሲንቀጠቀጥና ሲገዛ ይኖራል። በክርስቶስ ማን እንደሆነ ሲነገረውም #ለማመን ቢዘገይም የኤፌሶንን መልዕክት የመድሃኒት እንክብል መስጠት ተገቢ Treatment ይመስለኛል።
በክርስቶስ መሆኑን እርግጠኛ የሆነ ሁሉ የዚህ የክብር ህይወት ተካፋይ ነውና።

የኤፌሶንን መልዕክት ለማፍቀር የምንገደድበት ምክንያት በመንፈስ ወደ #ሰማያዊ_ስፍራ ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ነው። ከዚህ መልዕክት ውጪ በየትኛውም የመፅሀፍቅዱስ ክፍል ይሄ ቃል አይገኝም።
ዘላለማዊ ምሉዕ የቃልኪዳን በረከት ያገኘንበት ስፍራ ነው። ( 1÷3 )
ታላቁ #ሊቀ-ካህናችን ኢየሱስ : በአሁኑም በሚመጣውም ዓለም ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ የገነነ ስም ያለው ኢየሱስ : ንጉሱ ያለበት ስፍራ ነው። (1:19-21)
የመንፈሳዊ
ህብረት(Communion)ስፍራ(2:6)
ሀጥያት እንደ አውሎንፋስ ጠራርጎ አርቆ ቢወስደንም መስቀሉ ሰበሰበን። የማይረጋው ልቤ ከሚለኝ እግዚአብሔር በቃሉ ሚለኝን ብሰማ ይሻለኛል ላለ ... የምስራች በክርስቶስ እጅጉን ቅርብ ሆነን ከእርሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ ተቀምጠናል።
ልዩ ልዩ መለኮታዊ ጥበብ ለቤተ ክርስቲያን የሚገለጥበት ስፍራ(3:10)
የተሸነፈን ጠላት የምንዋጋበት: የድል ነሺነት የውጊያ ስፍራ። (6:12)

#ሌላው በኤፌሶን መልዕክት ውስጥ በተደጋጋሚ እየመጣ ሀሴት የሚሞላን አንድ #የተባረከ_ቃል አለ። ይህም #በክርስቶስ( በእርሱ, in Christ , through Christ , by Christ , for Christ & so on) በዚች ከ 6 ምዕራፍ በማትበልጥ መልዕክት ውስጥ ቃሉ ከ50 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል። መንፈስቅዱስ በቅዱስ ድርሰቱ ከ50 ጊዜ በላይ Remind ሊያደርገን የሚፈልገው ነገር በፀጋ የሆነልንና ተስፋ የምናደርገው ሰማያዊ ክብር ሁሉ በክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር ሊሰጠን የሚችለውን #ሁሉ በክርስቶስ ሰጥቶናል። #ነፍሱን_የሰጠን_ምንም_እንደማይከለክለን_አስረዳን።

#ያለ_ክርስቶስ የነበርንበትን Extreme ዝቅጠት አሳይቶ : እንዲህ ወዳለ አስደናቂ ክብር በክርስቶስ ተሻገራቹ ሲለን ከምስጋና ውጪ ምን እንላለን??
(Regeneration by Christ)

ይሄን አስደናቂ መልዕክት የሚፅፍላቸው ሐዋሪያው ጳውሎስ ሳይድን(የጠርሴሱ ሳውል) ሊያያቸው እንኳ ለማይፈልግ Pagan Gentiles :ሲድን ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ በኤፌሶን ወንጌል ሰብኳልና የጥል ግድግዳ በክርስቶስ ፈረሰ ሲል ያምርበታል። (Reconciliation by Christ )

#ታላቁ ሚስጥር እና አስደናቂው የጳውሎስ ፀሎት የሚደንቁ ሀሳቦች ሲሆኑ በመጨረሻም
Education of Grace
Excercise of Grace &
Exhortation of Grace ን በማብራራት መልዕክቱን ያጠናቅቃል።

እወዳችኋለሁ ተባረኩ
መልዕክቱን ያጋሩ

@untothelamb
@untothelamb
@untothelamn