Get Mystery Box with random crypto!

አረቦች አይደሉም ግና መግባቢያ ቋንቋቸው አረብኛ እንዲሆንላቸው ታግለዋል። በክርስቲያን ግዛት ውስጥ | ISLAM IS UNIVERSITY

አረቦች አይደሉም ግና መግባቢያ ቋንቋቸው አረብኛ እንዲሆንላቸው ታግለዋል። በክርስቲያን ግዛት ውስጥ ያሉ አናሳ ቁጥሮች ግና በኢስላማዊ ህግ በሸሪዓ ድንጋጌ መዳኘትን የጠየቁ በሒጃባቸው የፀኑ፣ ሰላታቸውን የማያዛንፉ ቋሚዎችና ጿሚዎች ናቸው።


በቁጥር ጥቂት ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ግን ግዙፍ ነው። የክርስቲያኖች ቁጥር ከ80 ሚሊዮን በላይ በሆነባት ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ከ15 ሚሊዮን የማይበልጡ ጀግኖች

የስፔንን ወረራ በመጋፈጥ የዘመቻውን መሪ የገደሉ!
ሀገራቸው ለአሜሪካዊያን በ20 ሚሊዮን ዶላር ተሽጦባቸው እጃቸውን ያልሰጡ!
ለተከታታይ 40 ዓመታት የአሜሪካን ወረራ ተቋቁመው እስልምናን መንካት ቀይ መስመር መሆኑን ያስተማሩ ፅኑዎች።

በ1972 ፊሊፒን የካቶሊክ ክርስቲያን ሀገር እንድትሆን ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ለቫቲካን ሊቀ ጳጳስ ቃል በገባላቸው መሠረት ሙስሊሞች ላይ ብዙ እልቂቶችን ፈፀመ። የግፍ በትሩ በየከተማው ተቀጣጥሎ መንደሮችን ዘልቆ በየቤቱ ደረሰ።

  ይህን ግፍ ለማስቆም የሞሮ ብሄራዊ ነፃ አውጪ የሙጃሂዶች ግንባር ወታደራዊ ጂሃድን አወጀ። ከ150,000 በላይ ሙስሊሞች ሸሂድነትን ተጎናፅፈው አፀደ ገላቸው ከጂሃዱ ሜዳ ስር አረፈ። በርካቶች ቆሰሉ። ብዙዎችም ሀገር ለቀው ተሰደዱ።

ከበርካታ የትግል አመታት በኋላ ድልን ተጎናፀፉ
   ኢስላማዊ እሴቶቻቸውን አያከብርምና ዓለማዊ አገዛዝን ውድቅ አደረጉ። ኢስላማዊ ህግ በሀገራቸው ተፈጻሚነትን ያገኝ ዘንድ ራሳቸውን በራስ ማስተዳደር ጀመሩ። የላኢላሀ ኢለላህ ዓርማ የሰፈረበትን ባንዲራ አውለበለቡ። ግና በውስጣዊ ሽኩቻ ነፃነታቸውን ዳግም አጡ።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2019 በተካሄደው ህዝባዊ ውሳኔ የራስ ገዝነታቸው ፀድቆ ሸሪዓ በስርዓተ ትምህርታቸው ላይ እንዲካተት ተወሰነ። በርካቶች ተገረሙ። አብዛኛው ነዋሪዎቿ ክርስቲያኖች በሆኑባት ከተማ የመስቀል ዓርማ በመንደሮቿና በአካባቢዎቿ በተተከለባት ሀገር ህዝበ ክርስቲያኑ በሙስሊሞች ህግ ለመዳኘት መወሰኑ እጅጉኑ አስደነቀ። "በእስልምና ውስጥ ፍትህና ፍቅር አጊንተናል" ሲሉ ነዋሪዎቿ ምስክርነታቸውን ሰጡ። ሸሪዓ ከህጋቸው ጋር እንዲካተት ታወጀ።

ይህ በዓለም ላይ እስልምና በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋበት ሀገረ ፊሊፒን ናት።