Get Mystery Box with random crypto!

ደስታውንና ሐዘኑን በእግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማ ስር ያደረገ በእርግጥም ከሰረ። ለኳስ የሚያነባ ዓይን | ISLAM IS UNIVERSITY

ደስታውንና ሐዘኑን በእግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማ ስር ያደረገ በእርግጥም ከሰረ። ለኳስ የሚያነባ ዓይን የሙስሊሞችን ቅዱስ ሥፍራ ነጻ ሊያወጣ ክብራቸውንም ሊያስመልስ ፈፅሞ አይቻለውም


ትራምፕ እየሩሳሌምን የጽዮናዊት ዋና ከተማ መሆኗን ለማወጅ ሲነሳ በምስሉ ላይ የሚታየው ህፃን በጽዮናዊው ወታደር ፊት በጀግንነትና በኩራት ቆሞ ይታያል

የህፃኑ ሁኔታ የነገን ምስል ያሳያል። እየሩሳሌምን ነፃ የማውጣት ተስፋ የኡማው እጣ ፈንታ እኔ ነኝ ይላል።

ከታች ያለው ምስል በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በግብፅ እና በኮንጎ መካከል በነበረው ግጥሚያ ኮንጎ በግብፅ እግር ኳስ ቡድን ላይ ጎል በማስቆጠሩ ወጣቱ እያለቀሰ ይታያል

ይህን ወጣት ሴቶች ሲያዩት ስለወደፊታቸው ሊሰጉ ስለደህንነታቸው ሊፈሩ ይገባቸዋል።

ኻሊድ አርራሺድ እንዲህ ይላል
"ይህ ትውልድ አቅሳን ነፃ እንዲያወጣ ትፈልጋላችሁን?! በፍፁም እንደውም የጠላቶች መሻገርያ ድልድይ፣ ልጓሟቸውን ይዘው የሚጎትቷቸው ባርያ ይሆናሉ። እንደነዚህ ዓይነቶቹ የኢስላምን ምሽጎች ለጠላት አሳልፈው ይሰጣሉ። የመስጂደል አቅሳን ቁልፍ ያስረክባሉ። እስልምና በልባችን ውስጥ ከሞተ የታል ጥንታዊ ኩራታችን የታለ ያ ውብ ኃያልነታችን?! ዋ በዲኔ ላይ ቁጭቴ! ዋ በወንድነቴ ላይ ቁጭቴ! በታላቁ አላህ እምላለሁ የትኛውም ህብረተሰብ በዚህ ሁኔታ ላይ ካደገ ለኢስላም ሊደነግጥ በፍፁም አይቻለውም። አይሁዶችና የመስቀል አምላኪዎች ማንነታችንን በመግፈፍ ላይ ተሳክቶላቸዋል። ዲን የለ ክብር የለ"