Get Mystery Box with random crypto!

በያዘው ፎጣ መኪናዬን እየጠራረገ 'የመኪናህን መስታወት ላፅዳውን?' በማለት ጠየቀ። ድንቡሽቡሽ ፊቱ | ISLAM IS UNIVERSITY

በያዘው ፎጣ መኪናዬን እየጠራረገ
"የመኪናህን መስታወት ላፅዳውን?" በማለት ጠየቀ። ድንቡሽቡሽ ፊቱ ችግር ያቆራመደው ይመስላል። በእጁ የጨበጠው ፎጣ መድረስ የሚፈልግበት ዓላማ እንዳለው ያሳብቃል። አንገቴን በመነቅነቅ በእሺታ ተስማማሁ።
  ስራውን በትጋት መስራቱ ስላስደሰተኝ 20 ዶላር ከኪሴ አወጣሁና ልሰጠው እጄን ዘረጋሁ። ብሯን በአግራሞት እያያት "ከአሜሪካ ነው እንዴ የመጣኸው?" ሲል ጠየቀኝ
"አዎ" አልኩት
"ከገንዘብ ይልቅ ክፍያዬ ስለ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ብትነግረኝስ?" አለኝ

  ለዕውቀት ያለው ጉጉት ስላስገረመኝ ተቀምጠን እንድናወራ የመኪናዬን በር እየከፈትኩለት
"ስንት አመትህ ነው?" በማለት ጠየቅኩት
"አስራ ስድስት" አለኝ
"የሁለተኛ ደረጃ የሀይስኩል ተማሪ ነሀ?!"
"በብዙ የትምህርት ዓይነቶች ጥሩ ውጤት ስላመጣሁ ሁለት ክፍሎችን ከፍ አድርገውኛል" አለ።
"እዚህ ፅዳት ስራ ላይ የተሰማራኸው ለምንድነው?" ስለው ትክዝ አለና
"አባቴ የሁለት ዓመት ልጅ እያለሁ ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለየው። እናቴ የሰው ቤት ምግብ አብስላ ተሰቃይታ አሳደገችን። እሷን ለማገዝ መኪና አጥቤ በማገኛት ገቢ ራሴንና እህቴን አስተምራለሁ። በተረፈኝ ብርም እማን እኻድምበታለው" አለና ሳግ እየተናነቀው ንግግሩን አቋርጦ "የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በአካዳሚክ ትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ስኮላርሺፕ እንደሚሰጡ ሰምቻለሁ ልትረዳኝ ትችላለህ?" አለኝ።
  "እሺ ግን መጀመርያ እንሂድና ምሳ እንብላ" አልኩት
"የመኪናውን የኋላ መስታወት ካጸዳሁልህ እሺ" አለኝና ተስማማን። ወደ ሬስቶራንቱ ዘልቀን ቦታችንን ይዘን ተቀመጥን። ከእናቱና ከእህቱ ጋር ለመመገብ ድርሻው ቴካዌ እንዲደረግለት ጠየቀ። የአነጋገሩ ለዛ እርጋታውና ቅልጥፍናው አግራሞትን ጫረብኝ።

  የምችለውን ሁሉ ልሞክርለት ቃል ገብቼ የትምህርት ሰነዶቹን ተቀብዬው ተሰነባበትን። ከስድስት ወራት በኋላ ስኮላሩ ተቀባይነትን አገኘ። እንኳን ደስ አለህ በማለት አበሰርኩት።
"በአላህ እምላለሁ ቤታችን በደስታ ለቅሶ ተውጦ እንባን እያረገፍን ነው" አለኝ።

ከሁለት ዓመታት በኋላ ስሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትንሹ ኤክስፐርት ሆኖ በኒውዮርክ ታይምስ መጽሔት ላይ ታትሞ ወጣ። በጣም ተደሰትኩ። ባለቤቴ ለእናቱና ለእህቱ በድብቅ ቪዛ አሰርታ አሜሪካ አስመጣቻቸው። ወጣቱ እናቱንና እህቱን በድንገት ሲያያቸው መናገርም ማልቀስም ተስኖት በድንጋጤም በደስታም ፈጠጠ።
አንድ ቀን ከቤተሰቤ ጋር ቤት ውስጥ ተቀምጠን መኪናዬን ሲያጥብ በመስኮት በኩል ተመለከትኩት
"ምን እያደረግክ ነው?" ስልም ጠየቅኩት
"የነበርኩበትን እንዳልረሳ አንተም ያደረክልኝን ውለታ እንዳልዘነጋ ነው" አለኝ

ስሙ ፈሪድ ዐብዱልዐሊ ይሰኛል ፍልስጤማዊ ወጣት ነው አሁን በአሜሪካ harvard (ሃርቫርድ) ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ካሉ ምርጥና ታዋቂ ፕሮፌሰሮች መካከል አንዱ ነው።

መልካምነት የተሰበሩ ልቦችን ጠግኖ ለስኬት ያበቃልና መልካም እንሁን።