Get Mystery Box with random crypto!

በታላቁ ሱልጣን ሱለይማን አልቃኑኒ የአመራርነት ዘመን በፈረንሳይ ውስጥ ሴቶች እርቃናቸው እየጨፈሩ | ISLAM IS UNIVERSITY

በታላቁ ሱልጣን ሱለይማን አልቃኑኒ የአመራርነት ዘመን በፈረንሳይ ውስጥ ሴቶች እርቃናቸው እየጨፈሩ ነው የሚል ዜና ኸሊፋው ዘንድ ደረሰ። በንዴት በግኖ ደብዳቤን ወደ ፈረንሳዩ ንጉስ ላከ፡፡

"በሀገራችሁ ያሉ ሀፍረት የሌላቸው ሴቶች እርቃናቸውን ከወንዶች ጋር ተቃቅፈው እየጨፈሩ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሀገራችሁ ከእኛ ድንበር ጎን ስላለች ይህ ጋጠወጥ ስነምግባር ወደእኛም ሊዛመት ይችላልና መልዕክቴ እንደደረሰህ ይህን እርኩስ ተግባር አስቁም። አለዚያ እኔው ዘምቼ ለማስቆም ጦሬን ሰብቄ ወደናንተው ሀገር እመጣለሁ"
ከዚህ ደብዳቤ በኋላ በሀገረ ፈረንሳይ ጭፈራው ለመቶ ዓመታት ሙሉ በምስጢርና በድብቅ ይከወን እንደነበረ የኦስትሪያው ታሪክ ጸሐፊ ሀመር ዘግቧል፡፡