Get Mystery Box with random crypto!

ስታድግ ፡ ፓይለት ሆነህ ፡ አንተ በምታበረው አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪ ሆኜ መካ ሄጄ ሀጅ ለማድረግ | ISLAM IS UNIVERSITY

ስታድግ ፡ ፓይለት ሆነህ ፡ አንተ በምታበረው አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪ ሆኜ መካ ሄጄ ሀጅ ለማድረግ እመኛለሁ ።

ይህ አንዲት የካሽሚር እናት ከአመታት በፊት ፡ ለልጇ የተመኘችው ነገር ነው ። እና ይህን ህልሟን በወረቀት ፅፋ አስቀመጠች ። የእናቷ ምኞትን ለማሳካት መንገዱን ሲጠርግ የቆየው ያያኔው ታዳጊ ልጇ አድጎ ፓይለት ሆነ። እና እናቱ እንደተመኘችው ራሱ በሚያበረው አውሮፕላን ፡ ወደ መካ ይዟት በመሄድ ሀጅ አደረገች።
ራእይህን ፡ ህልምህን ለማሳካት ከልብ የሆነ መሻትና ጥረት ካለ ያ ህልም እውን ይሆናል።