Get Mystery Box with random crypto!

'ዝንባሌ ' አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ! የዛሬው የምክር ፅሁፋችን ለየብቻችን ለራሳችን | ISLAM IS UNIVERSITY

"ዝንባሌ "

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ! የዛሬው የምክር ፅሁፋችን ለየብቻችን ለራሳችን የምንጠይቅው ርዕስ እንደሆነ ግልፅ ነው። ዘመናችን በአስተያየት በአመለካከት አረም የበዛበት ግዜ ነው። ይህ ሌሎች ትርጉሞች የመስጠት አቅም ቢኖረውም እዚህ ላይ ልንረዳ የሚገባን ነገር ሰዎች እንደመሆናችን መጠን አስተያየት እና ምልከታ ብሎም አመለካከት መኖራችን አይቀሬ ነው። ነገር ግን  ይህ በመለኪያ ሚዛን መመዘን ካቃተን ዝንባሌዎቻችን ከሚዛኑ በልጧል ማለት ነው።ልብ እንበል ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ መልዕክተኛ ሆነው ከአላህ ሲላኩ ሰዎች በመጀመሪያ የጥሜትን መንገድ የጀመሩት በዝንባሌያቸው መገታታቸው መሆኑ መረሳት የለበትም። እኛ 360 ጣኦታትን ትተን አንድን አምላክ እናምልክ እንዴ ማለታቸው ታላቁ የነሱ ዘመን መገለጫ ሲሆን በኛ ዘመን ደግሞ 360 ጣኦት በላይ ለመቁጠር አዳጋች በሆነ መልኩ በምክንያት የተረጋገጠ በሚመስል እውነታ በውስጡ እውነትን ሳይዝ ውሸት እውነት በመሰለ ጥሩነቱ በሀቅ ያልተመዘነ  ዝንባሌያችን  የኛ ዘመን ጣኦት መሆኑ እርግጥ ነው። ዝንባሌ እምነትን የመግለፅ አቅም አለው። ሁሉም ሰው በዝንባሌው ውሎ በዝንባሌው ያድራል። ያለ ዝንባሌ በህይወት የሚኖር ሰው የለም። ሁላችንም የእያንዳንዱ የቀን ውሏችን የምንውልበት መንገድ የኛን ዝንባሌ በምንውልበት ቦታ ይገለፃል። የምንማረው ትምህርት ዝንባሌያችንን ያመለክታ ዝንባሌያችን ግን በተግባር ይረጋገጣል። ስለዚህ ራሳችንን መመልከት ማለት ተግባራችንን እንጂ እውቀታችንን መሆን የለበትም። ምክንያቱም የምንተገብረው ተግባር ለተማርነው እውቀት ዝንባሌያችን የምንገልፅበት መሆኑን እንረዳ... እያንዳንዱ ሰው በራሱ ከሚውልበት ቦታ ሌሎችም ሌላ ቦታ ይውላሉ... ያድራሉ። ወደድነውም ጠላነውም.. ነገር ግን በምንውልበት ቦታ አላህን ማስታወስ እና የአላህን ተዕምር መመልከት ከዚያም ሱናቸውን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን መተግበር የቻለ ሰው ትልቁ ትክክለኛው የዝንባሌ ጣራ መሆኑን እንረዳ! ለዚህም ነው ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ያሉት ( ማናችሁም አላመም የውስጥ ስሜቱ እኔ ለመጣሁበት መንገድ ወዶ መከተል እስካልቻለ ድረስ...)  ብለዉ የወህይ ቃላታቸውን ለኛ የሰጡን...
ዝንባሌያችን ከየትኛው ይሁን!?

የቴሌግራም ቻናላችንን join ይበሉ ሌሎችም እንዲደርሳቸው ሼር ያድርጉት።
t.me//@mind_islam