Get Mystery Box with random crypto!

አሁን እኔ በምኖርበት ከተማ ደሴ ከባድ ሁኗል፡፡ ወሎየ የቆንጆ ሀገር እየተባለ Hiv ተስፋፍቷል፡፡ | ISLAMIC SCHOOL

አሁን እኔ በምኖርበት ከተማ ደሴ ከባድ ሁኗል፡፡ ወሎየ የቆንጆ ሀገር እየተባለ Hiv ተስፋፍቷል፡፡
በዚህ ሰሞን አንዲት ልጅ ብቻ ተረድታኝ ደሴ ላይ ትልቅ ስራ እየሰራን ነዉ ፡፡የሚገርማችሁ ከ9 እስከ 12 ክፍል ተማሪዎች hiv ያለባቸዉ በጣም ብዙ ናቸዉ ግን ራሳቸዉን የለብንም ብለዉ አሳምነዋል  እነሱን በምክር
መድሀኒት እንዲጀምሩ እያረገች ነዉ ያለችዉ አላህ እድሜዋን ይጨምርላት፡፡ የአዲስ አበባን አላቅም ሰፊ ስለሆነ ወሎ ጠቅላላ ከተሞች በተለይ ደሴ በጣም ልቅ ተሁኗል፡፡ የአሊሞች ሀገር ወሎ በፊት ድሮ ቀረ አሁን ወሎ የቆንጆ ሀገር እየተባለ ብዙ ሴቶች hiv እየተገኘባቸዉ ነዉ፡፡ በነገረችን ላይ አላህ ተዉበቱን ይስጣችሁ ሸይጧን አሳስቷችሁ ዚና ላይ የወደቃችሁ ወንድም ሴቶች ራሷችሁን ተመርምራችሁ ብታቁ ጥሩ ነዉ...ለወደፊት ሚዲያ ላይ መፃፍ ከቻልኩ የማሳዉቃችሁ ይሆናል ጊዜዉ ከብዷል...እኔ ለራሱ ደንግጬ ሂጄ ተመረመርኩ ..እናም hiv በመመርመር ራሳችንን ብናቅ ጥሩ ነው፡፡

እኔም ለወደፊት መስጊድ ኢማሞች ጋር መጅሊስ ድረስ ደርሶ ቋሚ የሆነ Hiv pos የሆኑትን የማገናኘት ስራ ወንዱ ራሱን እንዲያጋልጥ የማድረግ ጥረት እያረኩ ነዉ ኢንሻ አላህ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ አላህ ያሳካዉ

ልላችሁ የፈለኩት አሁን በhiv pos ሰሞኑን ለማገናኘት ጥረት ስናደርግ ያወኩትን ትዳር ማማረጥ ያበዛችሁ ሀሳባችሁ ለብራይድ ለሰርግ ብቻ የሆናችሁ ሴቶች በተለይ ከ22 አመት የሆናችሁ ሴቶች በምሳሌ በእዉነታ ላስረዳችሁ ብየ ነዉ ሰከን በሉ ..

እኔ የማቃቸዉ ብዙ ወንዶች አሉ ትዳር ይፈልጋሉ ግን የወር ገቢያቸዉ ከ4,000 እስከ 6,000 የሆነ ግን እንዴት ብለን እናግባ ?? የቤት ኪራይ አስቤዛ ወጥቶ  እንዴት ይበቃል ነዉ የሚሉት ወላሂ ከባድ ጊዜ ነዉ፡፡


የሚገርመኝ ሴቱ ሷሊሁን ኢማን ያለዉን ትዳር ስጠን ብሎ ዱአ ያረጋሉ አንዳንዴም ሰምታችሁ ከሆነ በመስጊድ መዋጮ ጥሩ ትዳር እንዲሰጠኝ ወርቄን ብሬን ሰጠሁ ይላሉ ..ግን በስንት ዱአ ባሉን ሲያገኙ የሰጡትን ወርቅና ብር በ10 አባዝተዉ ባላቸዉ እንዲሰጣቸዉ ይመኛሉ

የህንድ የቱርክ አማረኛ ፊልም ላይ ያለዉን ትዳር እርሱትና በኪራይ ቤት በአንድ ክላስ በ5000 ብር የወር ገቢ ያለዉ ጋር ለመኖር ራሳችሁን ብታዘጋጁ ይሻላል፡፡ካልሆነ ይሄ የኖሮ ዉድነት ወንዱ ትዳርን እየሸሸ ነዉ ያለዉ...
ለሚመጣዉ አመት የመንግስት ስራ ቅጥር የለም ተብሏል፡፡ በጣም ከባድ ነዉ ዩኒቨርስቲ ላይ ስራ ስንይዝ እንጋባለን የተባለ ቃል ኪዳን ፈረሰ ማለት ነዉ ጎበዝ....በተጨማሪ ወንድ 2016 የመንግስት ስራ ባገኝ አገባለሁ ያለ አያገባም ማለት ነዉ፡፡እናም ሴቶች በtiktok በyoutube በህንድ ፊልም በአማረኛ ፊልም ያያችሁትን ትዳር አትመኙ ሰከን ማለት ያስፈልጋል፡፡

ሴቶች እባካችሁ ባህሪያችሁ አቋማችሁ አንድ ይሁን እቤት ጨዋ አደበኛ ..ትቤት እዉጭ ደግሞ ሌላ ..ለትዳር የሚፈልጋችሁ ሌላ አይነት ባህሪ አታሳዩ ..እንደ እስስት የራስህን ባህሪ ሌላዉ ጋር መመሳሰል ለህሊና ከባድ ነዉ በቃ አንድ ባህሪ የማይቀየር ያዙ ይጠቅማችሆል ወንዱንም አታወዛግቡ


እዚህ ቻናል ያላችሁ  ከ6እስከ10 ክፍል ያሉ ሴቶች ልጆች እህት ያላችሁ በጣም ተከታተሉ ስለዚና ቦይ ፍሬንድ ሀራም መሆኑን አስተምሩ፡፡ምን ገጠመኝ መሰላችሁ የአክስቴ ልጅ 7ክፍል ተማሪ ነች ከክላሳ ልጆች ጋር ትግባባለች ጠይቂያት ስትነግረኝ እነሱ ክፍል 42 ሴቶችአሉ ከእነዚህ ዉስጥ 37 የሚወዱት ደብቀዉ የሚያወሩት boyfrind አላቸዉ፡፡
የሚገርመዉ የወንድ ቁጥር አናሳ ሁኖ እንዴት ብየ ሳስበዉ ሴቶች እወቂ አንቺን እወድሻለሁ እያለሽ የሚያወራሽ 5 ወይ 4 ሴት እወድሻለሁ ሊል ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ እናም ከ7-10 ያሉ ልጆች ጋር ይሰራ
ለምን የጉርምስና ምልክት የሚጀመርበት ስለሆነ፡፡
ማወቅ ያለብን ሴት ልጅ በ9 አመቷ የወር አበባ ታያለች ወንድ ደግሞ በ15 አመቱ ነዉ የዘፈር ፈሳሽ ማየት የሚጀመርዉ.. ተረዱኝ ይሄ ማለት በአመለካከት በአስተሳሰብ በስሜት ደረጃ የ6 አመት ሴት ልጅ ከ12 አመት ወንድ ልጅ ጋር እኩል ነች ማለት ነዉ፡፡ የ18 አመት ሴት ልጅ ከ24 አመት ወንድ ልጅ ጋር እኩል አስተሳሰብ አላት ማለት ነዉ...እናም ሴትን ልጅ 9 አመቷ ነዉ ወይም ገና 14 ወይ 15 አመቷ ነዉ ህፃን ነች ማለት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አኢሻ ረዐ ነብዩ ሰዐወ በስንት አመቷ እንዳገባች የምናቀዉ ነዉ እናም ሴቶች በእናታችን አኢሻ ረዐ እድሜ ከደረሰች ልጅ ነች ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ ለአቅመ ሂዋን ደርሳለች በኢትዮ ህግ 18 አመቷ በ2ተባዝቶ መሆኑን አንዘንጋ


አንድ ቤተሰብ አለ 10 ክፍል እግል ትቤት የሚማር እኔ የማቃት ጅልባቢስት ነች የምላቸዉ ስናያቸዉ ልብሱን ለብሰዉታል አንገታቸዉን ደፍተዋል ግን በቃ ስልካቸዉን ከፍታችሁ ብታዩት ሞዴላቸዉ ቲክቶከሮች ናቸዉ ..እነሱ እንደ ቲኩተከሮች ሰርተዉ አስቀምጠዉታል በቲክቶክ አይለቁት አላህን ሳይፈሩ ቤተሰብ ፈርተዉ ትተዉታል ግን ቤተሰብ ባይኖር እንደ ለቀቁት ነዉ የሚቆጠረዉ እናም እባካችሁ ሴትን ልጅ ስታሳድጉ  እንደ እህት ሁናችሁ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

ደግሞ አሁን ለሴቶች ትልቅ አደጋ የዚና መስፋፊያ
የሆኑት ጀመአ ,በጎ አድራጎት ማህበር, የቲም እንከባከብ, አሮጋዉያን እንደጉም,የተቸገረ እንርዳ የሚል ብዙ ኢስላማዊ ጀመአዎች በሁሉም ከተማ አሉ
..እኔ ስማቸዉን መጥራት አልፈልግም የአደባባይ ሀቅ ነዉ በየመስጊዱ በሁሉም ቦታ ከተሞች አሉ ሴቱ ወንዱ አንፀባራቂ ለብሰዉ ሴቱ የዉበት ዉድድር የወጣ ይመስል ተበጃጅቶ ..ጀመአችንን ለማጠናከር እየተባለ
☞ በየመንገዱ ሲዋክ መሸጥ
☞ ቡና እያፈሉ መሸጥ
☞ሴቶች የወንድ ጫማ እስከመጥረግ
☞ ወንድ ሂዶ ሴቷን..ሴቷ ደግሞ ወንዱን የሆነ ነገር ይዞ ግዛኝ ማለት
☞ ወንድ ባለበት ሱቅ 4ሴት ወይ ከዛ በላይ ሴት ያለበት ሱቅ ሰበብ ብሎ ወንድ እየሄዱ በይሉኝታ ብር መቀበል
☞ በየአዳራሹ ተቀላቅሎ መሰብሰብ
☞ የአረጋዉንያ ቤት ማፅዳት እየተባለ 6ሴት 3ወንድ እየሆኑ አብሮ መስራት መሳቅ ምን ይሉታል??
እኔ የሚገርመኝ የሴቶቹ አይደለም ወላሂ እናት አባት እህት ወንድም መንገድ ለመንገድ ስትገራፈጥ ስታሽካካ እያየ መፍቀዱ ነዉ..,
ቆይ እስኪ መንገድ ለመንገድ ለጀመአ ማጠናከሪያ እየተባለ ሲዋክ ወዘተ ከመሸጥ መጀመሪያ የእናት የአባት የጎረቤት የዘመድ ሀቅ ጠብቀሻል

ግልፁን ከተነጋገርን ይሄ ጀመአ አጅር የሌለዉ ንያዉ ሙሀላጣን የሚያስፋፋ የማወራትን ልጅ በምን መንገድ ላግኛት ካፌ ይሻላል ሌላ ቦታ?? ተብሎ ይታሰብ ነበር በፊት ዛሬ ግን በጀመአችን ወርሀዊ ስብሰባ የገቢ ማሰባሰቢያ ስም መገናኘት ነዉ ወዳጄ በኢስላም ስም ብዙ ካባ የለበሱ ስራዎች በዝተዋል፡፡ እኔ ጀመአ መቃወሜ አይደለም ግን የትኛዉ ነዉ ከሙሀላጣ የፀዳ ወንድና ሴት የማይቀላቀልበት አላህ ብለዉ የሚሰሩ??
ለአንድ ኪሎ ሩዝ የ10 ቤተሰብ ፎቶ ማንሳት ካሜራ ካልያዙ አይሰጡም..ለአላህ ብለዉ ያለካሜራ አይንቀሳቀሱ በቃ አለ አይደል የሆነ እስልምና በነዚህ ጀመአዎች ሲመዘን እንጃ ነገን ያስፈራል፡፡ እህቴ ሆይ በደንብ እሰቢበት ካለሽበትም አባል ከሆንሽም በደንብ እሰቡበት