Get Mystery Box with random crypto!

ቆይ ግን ምንድን ነዉ ነገሩ??        አሚር ሰይድ    በቃ መፃፍ መናገር አስጠልቶኝ ሰ | ISLAMIC SCHOOL

ቆይ ግን ምንድን ነዉ ነገሩ??
       አሚር ሰይድ

   በቃ መፃፍ መናገር አስጠልቶኝ ሰልችቶኝ ነገሮችን እያየሁ ከአቅም በላይ ሁነዉ ዉስጤ እየተቃጠለ ብዙ ነገሮችን እያለፍኩ እና በቻልኩት አቅም ከሚዲያ ርቄ በተቻለኝ  አቅም በቻልኩት ብቻየን እየሰራሁ ነዉ ግን አንድ እጅ አያጨበጭብም ግን አሁን ዘመን ካለ ሙስሊሞች ጋር የኢንሻ አላህና የአላሁ አክበር ከማለት ዉጭ ወደ ተግባር የማይሄዱ ጋር ከመስራት ብቻ መስራት ይሻላል፡፡

በቃ ለሴት የተጣመመ መጥፎ አመለካከት አለህ ምናምን ስድብ ወቀሳ ሲበዛ ከሚዲያ ራሴን አራኩ ግን በቃ ነገሮች አያስችሉም

ዛሬ ወረረኝ በቃ አለ አይደል በጣም ልቤን የነካኝ በጣም ያሳዘነኝ ነገር ገጠመኝና ለመፃፍ ተገደድኩ፡፡
በጂልባብና በኒቃብ ዙሪያ ከምር ከባድ ነዉ ..ጅልባብ ኒቃብ የሸፈናቸዉ ነገሮች እየከበዱ ትክክለኛ ለባሾችን በኛም በሙስሊሙ ለሌላም ሀይማኖት አያጋለጥናቸዉ ነዉ  እያዮቸዉም ነዉ ፡፡

!!!ሴቶች ሆይ እባካችሁ ከአረብ ሀገር ስትመጡ አትልበሱ በቃ ኢትዮ ኤርፓርት ስደርሱ አዉልቁትና ስታምኑበት ልበሱ...ሴቶች ሆይ ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል ኢማናችሁ ሲጨምር ወይም አንድ ሁለት ኪታብ ስትቀሩ ዲኑ የገባችሁ መስሏችሁ ኒቃብ ጅልባብ ለብሳችሁ አላህን የማይፈራ ሴት ጓደኛ ይዛችሁ ወይም የቱርክ ልብስ ወይም በራሳችሁ ሳይዝ አሰፍታችሁ መልበስ ስትፈልጉ ኒቃብን ጅልባብን አታሰድቡ እባካችሁ፡፡ ከለበሱ ቡሀላ ኢስላም ከሚሰደብ እባካችሁ በቃ አዉልቁትና እንደገና የጂልባብ የኒቃብ ትርጉሙ ጥቅሙ ሲገባችሁ ልበሱት፡፡
..,አላህን ፍሩ ማለቱ ከቃላት ማባከን ዉጭ ለዉጥ አላመጣም በቃ አላህን አታስቆጡ ዲነል ኢስላምን አታሰድቡ...ኢስላምን መጥቀም  ባንችል በኛ እንዲሰደብ ለምን እናደርጋለን???

ዛሬ ጁምአ የገጠመኝን ልንገራችሁ
እኔ የምኖርበት ሰፈር ቤተክርስቲያን በቅርብ አለ ጠዋት ስወጣ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ፀበል ሲያስጠቅሙ ሲገቡ እኔ ለስራ በጠዋት ነዉ ከቤት የምወጣዉ መቼም መንገድ የማያሳየዉ የለም አያቸዋለሁ፡፡ ጠዋት ጠዋት እየመጡ ሳገኛቸዉ እኔ አረ አላህን ፍሩ በቁርአን መጀመሪያ ሞክሩ የሚሰማ የለም ኢንሻ አላህ ብሎ ከማለፍ ዉጭ.. ግዴታ ማድረስ ስላለብኝ አይቶ ማለፍ ወንጀል ነዉ በቻልነዉ አቅም እናገራለሁ...

ዛሬ ያየሁት ግን በቃ ለአቅል ከበደኝ ሁለት ኒቃብ የለበሱ ሴቶች እኛ ሰፈር ያለ ቤተክርስቲያን እናታቸዉ ወይ ዘመዷን ይሆናል ይዘዉ ሲገቡ አየሁ ደነገጥኩ ...ግን ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲገቡ እዛ የነበሩ ሰዎች ስልካቸዉን አዉጥተዉ ፎቶ ሲያነሷቸዉ አየሁ   .. ወደ ቤተክርስቲያኑ አልገባ ጁምአ ነበር ጀለብያ ለብሻለሁ ጀለብያ ለብሼ ብገባ የነዛ ሰዎች ካሜራ ዉስጥ እገባለሁ ምን እንደሚያደርጉ ስለማይታወቅ...እስከምትወጣ ወደ 1 ሰአት ያክል ጠበኩ አልወጡም እኔም ከዛ አካባቢ ተንቀሳቀስኩ ... ዛሬ በአይኔ አየሁ ግን ከአሁን በፊትም ይገባሉ አላገጠምኝ ማለት ነዉ፡፡

እና ምንድን ነዉ ነገሩ???ሊታወቅልኝ የሚገባዉ ጅልባብ ኒቃብን ተቃዉሜ አይደለም ግን በጅልባብና በኒቃብ ጀርባ ብዙ ከኢስላም ያፈነገጡ ነገሮች አሉ... ትክክለኛ ኒቃብ ጅልባብ ለባሽ በነዚህ ፎርጅድ ለባሾች አብረዉ እየተወቀሱ አንገታቸዉን እየደፉ ነዉ፡፡


ከምር ጊዜዉ ከባድ ነዉ ብዙ የማቃቸዉ ወንዶች ኒቃቢስት ጅልባቢስት ነች ብየ አግብቻት እንዲህ እንዲህ ሆን እያሉ ብዙ ነገሮች እየሰማን አሁን ዘመን ላይም እያየን ነው...ያኒቃምን የጅልባብን  ትርጉሙን ሳያቁት የሚለብሱትም ግራ እየተጋባን ነዉ፡፡

አሁን ላይ እሷ ሷሊህ ነች ኢማን አላት ወይም ኢማን አለዉ ማለት ይከብዳል .. አፍ ሞልቶ የኔ ልጅ ወይ የኔ እህት እተማመንባታለሁ ማለት ከባድ ነዉ....እኔ እንደሚመስለኝ
ኢማን የሴት ልጅ..ሷሊህ የወንድ ስም ነዉ ወዳጄ ..እከሌ ኢማነኛ እሱ ሷሊህ ነዉ ማለት የማይቻልበት ዘመን ላይ ነን ..
ሷሊሀ ነች ሳይሆን በግልባጩ ጧሊሀ የሆነበት ተጨባጭ እያየን ነዉ፡፡


አሁን ሴቱ እሁድ ተጋብቶ ከወር ቡሀላ ብትፈታ ችግር የለባትም
ሀሳባቸዉ ብራይድ ሰርግ እንጂ ነገን ከነገ ወዳስ ትዳር ላይ እንዴት ነዉ ብለዉ ብዙዎች አያስቡም በተለይ ከ22 አመት በታች የሆነች ሴት፡፡
የሴት ኢማኗ የሚለካዉ ሰርጓ አካባቢ ነዉ በፊት ጅልባብ ለባሽ ኒቃብ ናቸዉ የተባሉት ለሰርጋቸዉ ኢማናቸዉ እንደ ወራጅ ወንዝ ወደ ታች ይፈሳል ልባቸዉ ላይ አይረጋም፡፡

የአማረኛ የቱርክ ፊልም እያዩ  በኑሮ ዉድነት እዳዉን ያየ ወንድ ሰርፕራይዝ ምናምን ነዉ ሀሳባቸዉ እንጂ ትዳሬ የምትል ሴት እንጃ እየጠፋች ነዉ፡፡ ወንዱም በሴቱ ባህሪ ማግባት ባለመቻሉ ዝሙት ላይ እየወደቀ ነዉ

አንድ ነገር ሴቶች ላስታዉሳችሁ ነገሮች አሁን ወንድን ልትረዱ አልቻላችሁም  የኑሮ ዉድነት
የክርስቲያን ወንድ በ6000 ደመወዙ ማግባት ይችላል፡፡ የሙስሊም ወንድ ግን ከሴቱ ፍላጎት አንፃር 12,000 ደመወዝ ይዞ ማግባት አይችልም፡፡
በነገራችን ላይ ፍቅር ወንድም ሴትም እወዳታለሁ እወደዋለሁ እንጂ ይወደኛል ትወደኛለች ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ብዙ ያፈቀረ ሰዉ በህይወትህ ምን ተሳስተሀል ቢባል ማፍቀሬ ነዉ የሚለዉ ፍቅር እወዳታለሁ እወደዋለሁ በሉ እንጂ ይወደኛል ትወደኛለች ብላችሁ ራሳችሁን አታሳምኑ በራሳችሁ ብቻ እርግጠኛ ሁኑ....

በተጨማሪ በዚህ 3ወር ዉስጥ Hiv positive የሆኑትን ትዳር ለማገናኘት በሚል ከእነሱ ጋር እየሰራሁ ወላሂ ከባድ ጊዜ ላይ ነዉ ያለነዉ...
አዲስ አበባ,ደሴ,ባህርዳር,ጎንደር,ጅማ,ድሬድዋ,አፋር ክልል,ኦሮሚያ ክልል
ወዘተ ከተማ ላይ ከተለያዩ ሙስሊሞች ነርሶች ጋር ለማገናኘት ጥረን ነበር፡፡
ከባድ ነዉ የሰማሁት ለአቅል የሚከብድ ነዉ
አዲስ አበባ ሆስፒታሎች ደሴ የተለያዩ ከተሞች ላይ ያሉት በብዛት ከወንድ ብዙ እጥፍ ሴቶች ናቸዉ፡፡

አዲስ አበባ የሚያገናኝ ጀመአ ነበሩ እነሱን ስጠይቅ እንኳን Hiv pos ወንድ ኖርማል ወንድ ሴቶችን ለማገናኘት ጀምረን ለትዳር ዝግጁ የሆነ ወንድ አጣን ነዉ ያሉኝ...አሁን አቋም ያለዉ ወንድ የለም የሚያጮልቅ የሚያደባ እንጂ ሴቱ በምላስ ፍቅር ተተብትቧል ግን መቼ ድረስ???

አሁን በተለይ ሴቶች hiv pos የሆኑ እኔ እንኳ አሁን ለማገናኘት የማቃቸዉ ብዛትና ከተለያዩ ሆስፒታሎች ያገኘሁት መረጃ አለቅል ስለሚከብድ ዝምታ ይሻላል..አሏህ ለነዚህ ሴት እህቶች ይድረስላቸዉ፡፡ የሚገርመዉ ብዙ hiv pos ወንድ ወጣት ገና ከ16-25 እድሜ ያለዉ ይበዛል እነሱ የሚሉት አቅም የለንም ነዉ፡፡ ደግሞ አቅም አለን የሚሉት ስናገናኝ 1ሳምንት አዉርተዉ  ስልካቸዉን ጥፍት በቃ ለምን በሴት ልብ እንጫወታለን???
Hiv pos የሆኖት ብቻ ሳይሆን ወንድ ሆይ!!! የትዳር process አገባሻለሁ እያልክ እድሜ ህልሟን ተስፋዋን አታጨልምባት ተስፋ አትስጥ ቶሎ ወስኑ ቀልብ አንስበር

ነገሮችን ስናጠና ወንዶች hiv ሲገኝባቸዉ ራሳቸዉን እየደበቁ በዚና ሴቶችን እያስያዙ እያገቡ እንደሆነ 90% እርግጥ ሁኗል፡፡