Get Mystery Box with random crypto!

በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ አንደሉስ ምድር መናገሻ ከተማ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ ጠዋት | ISLAMIC SCHOOL

በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ አንደሉስ ምድር መናገሻ ከተማ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ ጠዋት ነበር። ሰራዊቱ በፈረሶቻቸው ላይ ተፈናጠው በድካም የሚንጠፈጠፈውን ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠራረጉ አቧራ ባጨማለቀው ልብሳቸው ኢድ ወደ ሚሰገድበት ሜዳ በማቅናት ላይ ሳሉ ነበር አንዲት እድሜዋ የገፋ አዛውንት ከሡልጣን መንሱር ፊት ቆማ የፈረሱን ልጓም ይዛ ከመንገዱ በማስተጓጎል እንዲህ ያለችው:-


"በዛሬው የዒድ ቀን ከእኔ በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ደስተኞች ናቸው"
ሐጂብ መንሱር ንግግሯን ሲሰማ ደነገጠ "ለምን?" ሲልም ጠየቀ።
ዕንባ ባቀረረው ዓይኗ እየተመለከተችው እንዲህ አለችው "በረባህ ምሽግ ከመስቀል ጦረኞች ጋር ሲፋለም የተማረከ አንድ ፍሬ ሙጃሂድ ልጅ አለኝ እሱ በጠላት እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት መደሰት ይቻለኛል?"

ዘመኑ 380 ዓመተ ሂጅራ ግዛቶች በሐጂብ አል መንሱር ይተዳደሩ ነበር። የአንደሉስ ኢስላማዊ መንግስት በጥንካሬና በከፍታ ማማ ላይ የደረሰበት ወርቃማ ዘመን! የፉቱሐትና የዘመቻ የፍትህና የእኩልነት ጊዜ!

   ሐጂብ ንግግሯን ሲሰማ በፍጥነት ፊቱን ወደሠራዊቱ አዞረ። የፈረሱን ልጓም አጥብቆ ያዘና በጂሃድ ሜዳ የአፈር ትቢያውን ገና ላላራገፈው ሙጃሂድ፣ ከድካም ጀርባውን ላላሳረፈው ሠራዊት እንዲህ ሲል ትዕዛዙን አስተላለፈ "ከፈረሳችሁ ጀርባ እንዳትወርዱ" አለ።

   የፈረሱን ልጓም እየጎተተ ጀርባው ላይ እንደተፈናጠጠ ወደ ረባህ ምሽግ ሰራዊቱን ይዞ ገሰገሰ። የአሮጊቷን ልጅ ጨምሮ ሙስሊም እስረኞችን አስፈትቶ ከተማዋን በድል ከፍቶ ወደ አንደሉስ ምድር ተመለሰ።

ይህ ስለኢስላም መስራት በማንደክምበት ዕለት የተከሰተ የጀግንነት ታሪካችን ነው።


ለሁላችሁም ኢድ ሙባረክ ብያለሁ
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን....ከረመዷን በፊት ወደነበርንበት አመፅና ወንጀል የማንመለስ ያርገን
....ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን  ሩሀችን   እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን ያረብ

የቻናል ቤተሰቦች መልካም በአል ተመኘሁ