Get Mystery Box with random crypto!

ልብሽን ምክንያት እየሰጠሽ አታድክሚዉ ዩምና ሙሀመድ እራስሽን ልክ እንደ ሙሳ ቀይ ባህር | ISLAMIC SCHOOL

ልብሽን ምክንያት እየሰጠሽ አታድክሚዉ
ዩምና ሙሀመድ

እራስሽን ልክ እንደ ሙሳ ቀይ ባህር መሀል ላይ አኑሪው ከጀርባሽ ፊርአውንን እሚያክል ጠላት ወይ ችግር አለብሽ ከበላይሽ የተሰነጠቀ ባህር እሚያክል አንቺ ላይ ሊደርስ እሚችል ችግሮች ተከምረው ታይተውሻል ወደ ጎን አትይም መካከል ላይ ነሽ ብቻሽን አይደለሽም በአንቺ ስር ያሉ የብዙዎችን ህይወት ከአላህ በታች ይዘሻል ....ልክ ሙሳ ተከታዮቹን እንደያዘው ነፍሴን ብቻ አይልም ነፍሳችንን እንጂ ከእራሱ ሩህ በላይ እሚያስጨንቀው የተከታዮቹን ነገር ነው ምናልባትም አንቺ የብዙ ሀላፊነት ባለቤት ሆነሽ ይሆናል፡፡

ታዲያ ሙሳ ከባህሩ አልወጡምን? በየትኛው መንገድ? ከፊት ለፊታቸው በምትታያቸው አንድ መንገድ ያቺን መንገድ እስኪያገኟት ድረስ ወደ ሗላ አልዞሩም ወደ ሗላ ችግራቸው ነው ያለው ፊት ለፊታቸው ግን ነፃነት ከብዙ የነፍሶች ሀላፊነት ማረፍ ሀቀኝነትን ብቻ ቡዙ ተአምሮችን ይዟል ያቺ የታየቻቸውን መንገድ በጀሊሉ ፍቃድ ደረሱባት ዞር ብለው ወደ ችግሮቻቸው ሲያዩ ግን ቢወርድ ሊያጠፋቸው እሚችለው ባህር ሲከተላቸው የነበረውን ችግር ድምጥማጡን አጠፋላቸው

አንቺም ያሉብሽን ችግር እስክታልፊያቸው ዞረሽ አትመልከቻቸው ይደርሱብኛል እምትያቸው ችግሮችሽ ምናልባት የደረሱብሽን ችግሮች ማጥፊያ ናቸው ፡፡ መውጫሽን ተመልከቺ ግን ስለሁሉም ጌታሽን አጥብቀሽ ያዢው በእሱ ያለሽ እምነት ከልብሽ አድርጊው የተፃፈልሽ ሙሲባ በሙሉ ሊስትሽ አልነበረም የሳተሽ በሙሉ ሊያገኝሽ አልነበረም ልብሽን ምክኒያት እየሰጠሽ አታድክሚው

☞ አንቺ ማለት ሳትጠይቂው ለእሱ ባሪያው እንድትሆኚ የፈጠረሽ ባሪያው ነሽ
☞አንቺ ማለት ከስንት ሚሊዮን እህት እና ወንድሞችሽ ተመርጠሽ የተፈጠርሽ ፍጡር ነሽ
☞አንቺ ማለት በዱንያው እሳት ፈትኖሽ እንደ ወርቅ ሊያስከብርሽ ሊያስወድድሽ እሚያደርግ ጌታ ነው ያለሽ

>>> እናም ያኡኽታ ረህማኑን አጥብቂው የተጣበቀብሽ ይለቅሻል