Get Mystery Box with random crypto!

ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ (Exit Exam) ሞዴል ፈተና መሰጠት ተጀመረ። ሚያዚያ 25/2015 | Injibara University

ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ (Exit Exam) ሞዴል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ሞዴል ፈተና መስጠት የተጀመረ ሲሆን የሞዴል ፈተናው ለዋናው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በቂ የሆነ ዝግጅት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሞዴል ፈተናው አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት እና በምንድህስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ አስተባባሪነት ከዛሬ ሚያዚያ 25 እስከ 30/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ዋናውን መውጫ ፈተና ያለምንም ችግር እንዲፈተኑ የሚያስችላቸው መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ሀብታሙ ዘገዬ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የፈተና ሂደቱ ተመራቂ ተማሪ ባላቸው ኮሌጆች ሥር በሚገኙ ትምህርት ክፍሎች አማካኝነት ፈተናው ከተዘጋጀ በኋላ ወደ ኮምፒውተር ሲስተም ገብቶ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል የመውጫ ፈተናን በአግባቡ እንዲፈተኑ ለማድረግ ስልጠናዎች እና የተለያዩ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል፡፡

የሞዴል ፈተናው በቀጣይ ጊዚያት በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተዘጋጅቶ ከሚሰጠው ከዋናው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ቀድሞ መሰጠት መቻሉ በፈተናው የአሰራር ሂደት ዙሪያ በቂ ልምምድ እንዲኖረን ከማስቻሉም በላይ ተሸለ የሥነ-ልቦናና የክህሎት ዝግጅት እንዲኖረን ያደርጋል ሲሉ የሞዴል ፈተናውን እየወሰዱ የሚገኙ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡