Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2015ዓ.ም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2015ዓ.ም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኞች የእግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ባለቤት ሆነ፡፡

ከሚያዚያ 17-24/2015 ዓ.ም በአገው ግምጃ ቤት ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ስፖርት ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ዩኒቨርሲቲው በእግር ኳስ ጨዋታ አንከሻ ወረዳን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በርካታ የስፖርት ቤተሠቦች በተገኙበት እና በአገው ግምጃቤት ሁለገብ ስታዲየም በተካሄደው በእንጅባራ ዩንቨርስቲና የአንከሻ ወረዳ የእግር ኳስ ቡድኖች የዋንጫ ጨዋታ ከፍተኛ ፋክክር ተደርጎበት እንጅባራ ዩንቨርስቲ የእግር ኳስ ቡድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ጨዋታው በጥላሁን የኔው ቡድን መሪነት ሲካሄድ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ተጫዋች እና አምበል አዲሱ ሙሉቀን የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እንዲሁም የቡድኑ አሰልጣኝ መምህር አማረ መብራት የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የቮሊቮል የፍጻሜ ጨዋታ 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሙሉቀን ማሩ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተሸላሚ ሆኗል። በተመሳሳይ በጠረጴዛ ኳስ ጨዋታ ደግሞ በይበልጣል ጥላሁን አማካኝነት 2ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በውጤቱ መሰረት ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚደረው የአማራ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ስፖርት ውድድር ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ