Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ እና | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ እና  የሥራ ጉብኝት በማደርግ ላይ ይገኛሉ።

ከሚያዚያ 29/2015 ዓ.ም  ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በአሜሪካ የሥራ ጉብኝት የሚያደርጉት ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት  የሚያከናውናቸውን ተግባራት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመገኘት ለኢምባሲው የሥራ ኃላፊዎች ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን በአሜሪካ ካሉት ተቋማት ጋር በማገናኘት እና በማስተሳሰር የዩኒቨርሲቲው  ዓለምአቀፍ ትስስር እንዲጠናከር አምባሲው  እንዲያግዝ ለኤምባሲው ጥያቄ አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኢምባሲ አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ  እና ምክትል አምባሳደር ዘላለም ብርሃን እንዲሁም የዲያስፓራ ጉዳዮች ኃላፊ  አቶ አቻሜለህ ሙላት  እና የፐብሊህ ዲፕሎሚሲ ኃላፊ አቶ ነጋልኝ መኳንንት  እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀው  ኢምባሲው የዲያስፓራ አባላትን በማስተባበር ጭምር  እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች  ጋር  ለማስተሳሰር  አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። 

ፕሬዝደንቱ በሥራ ጉብኝታቸው ሌሎች ዩኒቨርስቲዎችንም በማግኘት ትስስር ለመፋጠር  እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን ለማዳበር የማስተዋወቅ ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ግንቦት 5/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ