Get Mystery Box with random crypto!

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሥነ ልቡና ዝግጅት (Psychological readiness) ላ | Injibara University

ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሥነ ልቡና ዝግጅት (Psychological readiness) ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ በሚያደርጉት ዝግጅት በራስ የመተማመን ብቃታቸውን የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው ሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል የተዘጋጀው ስልጠና ዋና ዓላማው የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በቂ የሆነ የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በማስቻል በራስ የመተማመን ባህላቸውን ከፍ በማድረግ ፈተናውን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስራት እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን የትምህርት ክፍል ኃላፊው መምህር ሙላት አራጋው አስረድተዋል።

በፈተና ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አሉታዊ ስሜቶችን ቀድሞ መከላከል፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ ሳይንሳዊ የአጠናን ስልት፣ እንዲሁም ፈተና ወለድ ጭንቀትን መቀነሻ መንገዶች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ የሚሉ ርዕሰጉዳዮች በስልጠናው ተዳሰዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ሳይኮሎጅ መምህራን የሆኑት ሙላት አራጋው፣ ሙሉዓለም አለማየሁ፣ ጥላሁን ፈንቴ(ረ/ፕ)፣ ፈንታሁን እንዳሌ፣ አበባው የኔነህ፣ አድምጠው አበበ፣ እርቂሁን አለምነህ እና ሽመልስ አያልነህ ሲሆኑ በሁሉም ኮሌጆች ስር የሚገኙ የመውጫ ፈተናውን ለመወሰድ በዝግጅት ላይ ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት የተሰጠው ስልጠና በቀጣይ ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ሚያዚያ 22/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ