Get Mystery Box with random crypto!

የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት የምርምር ሙከራ ተካሄደ። ////////// የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት | Injibara University

የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት የምርምር ሙከራ ተካሄደ።
//////////
የተሻሻለ የድንች ዘር ብዜት የምርምር ሙከራ ሥራው የተሻለ ምርታማነት ያላቸው የድንች ዝርያዎችን በአካባቢው በማላመድ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የማድረግ እሳቤ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ሚያዚያ 19/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) የምርምር ሥራውን በቦታው ተገኝተው በጎበኙበት ወቅት የምርምር ሙከራ ሂደቱን በየወቅቱ በመከታተልና በመገምገም ውጤታማነቱን የማረጋገጥ ተግባሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የምርምሩን የሙከራ ተግባር እያካሄዱ የሚገኙት የዕፅዋት ሳይንስ መምህር አቶ ዘላለም ካሳ እና የሆርቲካልቸር መምህር አቶ አዲሱ ሙሉቀን ሲሆኑ “ጉደኔ” እና “በለጠ” በተባሉ ሁለት የድንች ዝርያዎች ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የምርምር ሥራ የአርሶ-አደሩን የዘር ፍጆታ ለመቀነስና የዘር ብዜትን በመጨመር የተሻለ ምርትን ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም እነዚህን ሁለት የተሻሻሉ የድንች ዝርያዎችን አንዱን ለሁለት በመቁረጥ የተሻለ ምርትን ለማግኘት እና ለዘር ብዜት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የምርምር የሙከራ ጣቢያ በመትከል እና ሂደቱን እስከመጨረሻው በመከታተል ሊያስገኙ የሚችሉትን የተሻለ የንፅፅር ውጤት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ሥራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0ieygj6p9tkF6wDN5kvSxmRGTCbYbH9HSiGeWTeaZLjsehPvJD7iRBxdvzXb3S4qfl/?app=fbl