Get Mystery Box with random crypto!

ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ። በ2015 ዓ.ም ወደ እንጅባራ | Injibara University

ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ።

በ2015 ዓ.ም ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚተገበሩ ህግና ደንቦች ላይ ያተኮረ ገለፃ ተደርጓል፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ዲን የሆኑት ጌታየ ሙሉጌታ ገለፃው ዩኒቨርስቲው በዚህ ዓመት ለተቀበላቸው የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የማሻሻያ ትምህርት ከመጀመራቸው በ4ወር በግቢ ቆይታቸው ስለሚኖራቸው እንቅስቃሴ ያተኮረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ዲኑ አያይዘውም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን በአግባቡ ተከታትለው በስኬት እንዲያጠናቅቁ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ህግ እና ደንብ በማክበር መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የቤተ መጽሃፍት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የኔወርቅ በላይነህ የቤተ-መጽሐፍት አጠቃቀም ህግና ደንቦች፣ በላይ ዘለቀ (ዶ/ር) የተማሪዎች መኝታ እና ምግብ አገልግሎት አሰራር ሂደት ላይ የተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

መጋቢት 6/2015ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ