Get Mystery Box with random crypto!

የፋይናንስ ስርኣቱን ለማዘመን የሚያስችል የተደራጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Inte | Injibara University

የፋይናንስ ስርኣቱን ለማዘመን የሚያስችል የተደራጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Integrated Financial Management Information System) “IFMIS” ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት “IFMIS” ሀገር አቀፍ ፕሮጀክት ሲሆን መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ ለማስቀመጥ፣ በእቅድ ለመመራት እና የፋይናንስ ስርዓቱን ከንብረት፣ ከግዥ እና ከሰው ሀብት ጋር አቀናጅቶ ለመስራት እንዲሁም ዓመታዊ ፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን ለማሻሻል የሚያስችል፤ ወጪን በመቀነስ ጊዜን እና ጉልበትን የሚቆጥብ ስርዓት ነው፡፡
የውይይቱ መነሻ ሀሳቡ የቀረበው የገንዘብ ሚኒስተር ልዑካን በሆኑት በአቶ ዳንኤል ቸርነት አማካኝነት እንዲሁም አቶ ሰሎሞን ከበደ ደግሞ የዘመነ ፋይናንስ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚተገበሩ የአይ.ሲ.ቲ መሰረተ ልማቶች እና ኔትወርክ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) የፋይናንስ ስርዓቱን ማዘመን አስፈላጊ በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲያደረግ እና ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲሟሉ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች ዳብሮ ውይይቱ ጠጠናቋል፡፡
መጋቢት 7/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ