Get Mystery Box with random crypto!

'ለሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት፣ መምህራ | Injibara University

"ለሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት፣ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ፡፡
////////////

ሀገርን ለመገንባት እና ህዝቦችንም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር በየደረጃው የሚካሄዱ ውይይቶች አስፈላጊ መሆኑን እና የምሁራንም ሚናም ጎልቶ መታየት እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል።

በዛሬው እለት በተካሄደው ውይይት ለመምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች በሀገር ግንባታ ላይ ያተኮረው ሰነድ ቀርቧል። ከመምህራንም ለሀገር ግንባታ ግብዓት የሚሆኑ በርካታ አስተያየት እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መንግስት ሰላምን በማስፈን የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ (ህግ ማስከበር) ኃላፊነት እንዲወስድ፣ የሀገር ኢኮኖሚን ማሳደግ እና የኑሮ ውድነት እንዲያስተካክል፣ በተለያዩ ጊዜያት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ሲቀርቡ የቆዩ የደመወዝ እና ጥቅማ ቅጥም ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጥ እንዲሁም የተቋማት ግንባታ፣ የሚዲያ ነጻነት፣ የትምህርት ጥራት ችግሮች፣ ህገ- መንግስት የማሻሻል እና የሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያተኮሩ ነጥቦች ተነስተዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0WT88wFD2qEQXB3LmSvAWVQFnH7a4ZjRYnB3r2iMA8pJHh3K6u2yMasybvm2vVQXKl/?app=fbl