Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰሠራተኞች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ጉብኝት አደረጉ፡፡ ------------ | Injibara University

የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰሠራተኞች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ጉብኝት አደረጉ፡፡
------------
በጉብኝቱ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝደንት ወሀቤ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ተልኮ አንፃር በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች የተከናወኑ ተግባራትን መሠረት አድርገው ገለፃ አድርገዋል።
በተጨማሪም የአረንጓዴ ልማት፣ የእንስሳት ምርምር ጣቢያ፣ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ምቹ የሥራ ከባቢ በመፍጠር የህፃናት ማቆያ ማዕከል እና የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስላለው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለጎብኝዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ወሀቤ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አጋር ድርጅቶች ጋር የተለያዩ የውል ስምምነቶችን(MOU) በመፈራረም በመማር መስተማር ነጻ የትምህርት እድልን በማመቻቸት፣ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠትና ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባር ተኮር የሆነ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ለጎብኝዎቹ አብራርተዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት የአማራ ክልል ምክርቤት ህንጻ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዓለም ይታየው እንደተናገሩት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእድሜው አጭር ቢሆንም አስገራሚ ለውጥ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው ምክር ቤቱ ከዩኒቨርሲተው ጋር በተለያዩ ዘርፎች ለመስራት ዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በጊዜው አበበ እና በዩኒቨርሲቲው የሆርቲካልቸር ትምህርት ክፍል ኃላፊና መምህር የሆኑት እጅጉ ጥላሁን ዩኒቨርሲቲው በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ በግቢ ውስጥ እና ከግቢ ውጭ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ለጎብኝዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ታህሳስ 22/2015ዓ.ም