Get Mystery Box with random crypto!

የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ና አካል ጉዳተኞች ቀን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡ “ራሳችንን እናስመር | Injibara University

የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ና አካል ጉዳተኞች ቀን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ፡፡

“ራሳችንን እናስመርምር፤ ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ኤች. ኤ.ቪን እንግታ” በሚል መሪቃል የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ፣ እንዲሁም “የፈጠራ ሥራ ሽግግራዊ መፍትሄ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ተደራሽነት” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ በልዩ ልዩ መርሐ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ደብሪቱ ምናየሁ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ኤች.አይ.ቪ ኤድስ በሀገራችን እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቅሰው የወረርሽኙን ስርጭትን ለመግታትና ለመቆጣጠር እንዲሁም የአካል የአካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም የመሪነት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት ላይ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እየታዬ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ማህበረሰቡ ስለአካል ጉዳተኞች ያለውን አመለካከት እንዲቀየር ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የህክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቃል-አብ እሱባለው በጽሑፋቸው የኤች.አይ .ቪ ኤድስ ሥርጭትን ለመከላከል በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል። የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ሀብታሙ አለምነህ በበኩላቸው ደግሞ ማህበረሰቡ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ስላለው አመለካከት አካል ጉዳተኞችን ወክለው ዘርዘር ያለ ሙያዊ ማብራሪያ የያዘ ፅሑፍ አቅርበዋል፡፡
ኅዳር 23/2015 ዓ.ም