Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእንጅባራ ከተማ ለሚገኙ አትሌቶች የትጥቅ ድጋፍ አደረገ፡፡ የእንጅባራ ዩኒ | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእንጅባራ ከተማ ለሚገኙ አትሌቶች የትጥቅ ድጋፍ አደረገ፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ በእንጅባራ ከተማ ለሚገኙ 40 አትሌቶችና ለ2 አሰልጣኞች 480 ሽህ ብር ግምት ያለው የትራክ መሮጫ ጫማና የልምምድ ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸዉ ወርቁ (ዶ/ር) በልምምድ ቦታው ተገኝተው ድጋፉን ባስረከቡት ወቅት ዩንቨርሲቲው ስልጠና ከሚሰጥባቸዉ ዘርፎች አንዱ የስፖርት ትምህርት ክፍል መሆኑን ጠቅሰው ይህን የትምህርት ክፍል ለማጎልበት በግቢ ከሚሰጠዉ ስልጠና በተጨማሪ በእንጅባራ ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ ተሰጥኦ ያላቸዉን አትሌቶች መደገፍና ማበረታታት የሁልጊዜ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በዚህ ተግባር ስንበረታ ሀገራችንን በዓለም አደባባይ ሰንደቋን ከፍ የሚያደርጉ አትሌቶችን ማፍራት እንችላለን ብለዋል፡፡
የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸዉ ጥላሁን በበኩላቸላው በእንጅባራ አትሌቲክስ ክለብ ጥሩ ዉጤት ያላቸዉ አትሌቶችን ከማፍራት አንጻር ከተማ አስተዳደሩ እያገዘ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ድጋፍ ግን እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዩንቨርውቲዉ ይህን በጎ ተግባርም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
አሰልጣኝ አሸብር አንበሉ እንደገለጹት የልምምድ ቦታ፣ የዉድድር መሮጫ ትጥቅ/አልባሳት የመሳሰሉትን ችግሮች ከመቅረፍ አንፃር ዩንቨርሲቲው ባደረገላቸው ድጋፍ ችግራቸው መቀረፉን አንስተው የተሻለ ልምምድ በማድረግ ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
Injibara Communication.