Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ሰበር ሰበር | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ሰበር ሰበር ሰበር

አሁን ከምሽቱ 3:30 አካባቢ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 አካባቢ እየተደረገ በነበረ ከባድ የቶክስ ልውውጥ በተራዊህ ሰጋጅ ወንድሞቻችን ላይ በሁለቱ ላይ የቦምብ በአንዱ ደግሞ የጥይት ጥቃት የደረሰ ሲሆን አንደኛው ወንድማችን አሁን ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ።

ተፃፈ በ የጎንደር ሙስሊሞች ድምፅ
መጋቢት 22/2016 አ ል
=
የነዚህ ሰዎች ትግል ግን አይገርማችሁም? አጣብቂኝ ውስጥ ባሉበት ሰዓት ሙስሊሙ ላይ የማያባራ ጥቃት ካደረሱ ተሳክቶላቸው አገር ቢቆጣጠሩ ምንድነው የሚያደርጉን? ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ እነዚህን በኢስላምና በሙስሊሞች ጥላቻ የታወሩ አካላት የሚደግፉ ሙስሊሞች መኖራቸው ነው። ችግሩ ምን ሲደርስ ይሆን የሚነቁት?

ማሳሰቢያ፦

1- በጎንደርም ይሁን በሌሎች ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ያላችሁ ወገኖች በዚህ ወቅት ለምን የተራዊሕ ሶላቱ አይቀርባችሁም? ተጨማሪ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ፈጥናችሁ ብትወስኑ መልካም ነው።
2- ሌሎቻችን ደግሞ ሼር በማድረግ ድምጻቸውን ብናስተጋባላቸው መልካም ነው። ዱዓም እናድርግላቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor