Get Mystery Box with random crypto!

የወር ደሞዝተኛ ዘካ ~ የወር ደሞዝተኛ ገንዘብ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሲያሟ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የወር ደሞዝተኛ ዘካ
~
የወር ደሞዝተኛ ገንዘብ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሲያሟላ ነው።

① ለዘካ መነሻ መጠን (ኒሷብ) ሲደርስ።
ከኒሷብ በታች የሆነና በየጊዜው ወጭ የሚደረግ ገንዘብ ዘካ አይመለከተውም።

② ኒሷብ ከደረሰ በኋላ አመት ሲቆይ። አመት ያልሞላው ከሆነ መጠኑ ከፍ ያለ ቢሆንም ዘካ የለበትም።

ስለዚህ ለዘካ መጠን ደርሶ አመት ሲሞላው ዘካ ያወጣል። ለማውጫ ጊዜ ይሆነው ዘንድ አመቱ ከሞላ በኋላ በራሱ አንድ ቀን መርጦ ይወስናል። ከዚያም እስከ መጨረሻው ወር ከተጠራቀመው አጠቃላይ ገንዘብ ላይ 2•5% ያወጣል።

ውስብስብ አሰራር ውስጥ ከመግባት በዚህ መልኩ መጠቀም የተሻለ ነው። ወላሁ አዕለም።
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል
t.me/IbnuMunewor