Get Mystery Box with random crypto!

#የተፈጥሮ_ዑደት በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ ድል ማድረግም ሆነ ድል መሆን የሚባሉ ነገሮች የሉም። ያለ | የስብዕና ልህቀት

#የተፈጥሮ_ዑደት

በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ ድል ማድረግም ሆነ ድል መሆን የሚባሉ ነገሮች የሉም። ያለው እንቅስቃሴ ብቻ ነው:: ክረምት ከሁሉም የበላይ ሆኖ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ ይጣጣራል:: ሆኖም ጊዜውን ጠብቆ የፀደይን ተተኪነት ከመቀበል በቀር አማራጭ አይኖረውም፡፡ ፀደይም አበቦችን እና ፍካትን እንዲሁም ደስታን ይዞ ከተፍ ይላል። በጋውም ቢሆን ሞቃታማ ቀናቱን ለዘለዓለም ለማዝለቅ መውደዱ አይቀርም:: ነገር ግን የበልግን መምጣት ተቀብሎ ስፍራውን አስረክቦ ዘወር ይላል:: በልግም ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ እድል ይሰጣታል::

አጋዘን ሳርን ብትበላም እርሷ ራሷ የአንበሳ ምግብ ናት:: ይህ የጥንካሬ ጉዳይ አይደለም:: ማን ይበልጥ ይበረታል ስለማለትም አይደለም:: ይልቁን አምላክ የሞትንና የትንሳኤን ዑደት ለእኛ የሚያሳይበት መንገድ ነው:: በዚህ ዑደት ውስጥም አሸናፊም ተሸናፊም የለም:: መታለፍ ያለባቸው ደረጃዎች ብቻ እንጂ። የሰው ልጅ ልብ ይህንን እውነታ ሲረዳ ነፃ ይሆናል፤ አስቸጋሪ ወቅቶችን ለማለፍ አያዳግተውም፤ በድል አድራጊነት የሞቅታ ስሜትም አይታለልም:: ሁለቱም አላፊ መሆናቸውን አይዘነጋም:: አንዳቸው በሌላቸው ይተካሉ::

ዑደቱም ይቀጥላል::

ስለዚህ የፍልሚያ ቀለበት ውስጥ ያለ ቡጢኛ (የራሱ ምርጫ አሊያም ሊመረመር የማይችል እጣ ፈንታ እዚያ ያስገኘው) ከፊት ለፊቱ በሚጠብቀው ፍልሚያ ተስፋ በደስታ ስሜት ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፡፡ ክብሩንና ግርማውን መጠበቅ ከቻለ ፍልሚያውን ቢሸነፍም እንኳ ተሸናፊ ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም መንፈሱ ምንም አልተሸራረፈምና።

ስለደረሰበት ነገር ሁሉ ሌሎችን መውቀስን ሙጥኝ አይልም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍቅሮ፤ የፍቅር ጥያቄው ውድቅ ከተደረገበት
ጊዜ አንስቶ ይህ ውድቀት በእርሱ የማፍቀር ችሎታ ላይ ያመጣው አሉታዊ ለውጥ እንደሌለ ያውቃል::

በፍቅር ውስጥ እውነት የሆነው ሁሉ በጦርነት ውስጥም ይሰራል።

ፓውሎ ኮሆልዮ
@Human_Intelligence