Get Mystery Box with random crypto!

የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ! ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ | የስብዕና ልህቀት

የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ ሁኔታ ወይም ልምምድ ምክንያት ከደረሰብን ቀውስ የተነሳ በትክክል ማሰብ፣ መስራት፣ መተኛትም ሆነ መኖር እስከማንችል ድረስ የደረሰውን ሁኔታችንን እንደገና ወደቀድሞው ጤናማ ሁኔታ ማስመለስ ማለት ነው፡፡

•  የጎዳችሁና እስክትበቀሉት ድረስ ውስጣችሁን የሚያናድደው ሰው የወሰደባችሁን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  ሰዎችን አምናችሁ በተወሰደባችሁ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ምክንያት ዘወትር ከመቆጨታችና ከመቆዘማችሁ የተነሳ የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  አፍቅራችሁ ትንሽ ከተጓዛችሁ በኋላ ያ ሰው ለእናንተ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ብትደርሱበትም ካላችሁ የስሜት ትስስር የተነሳ ልትረሱት ባልቻላችሁት ሰው የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!  

•  ማንኛውንም ሰውም ሆነ ሁኔታ ከመፍራታችሁ የተነሳ ወደፊት መራመድ እስከማትችሉ ድረስ በመሆናችሁ ምክንያት የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

ወደራሳችሁ ተመለሱ! ወደቀደመው ሰላማችሁ ተመለሱ! ወደእውነተኛው ማንነታችሁ ተመለሱ! ከምንም ሁኔታና ከማንም ሰው ጫና ውጪ ወደነበራችሁበት ሚዛናዊ ሕይወት ተመለሱ!

ንቁ! ወስኑ! ምክርና እገዛን ፈልጉ! የድሮውን ጤናማ ማንነታችሁን እንደገና የራሳች አድርጉ እንጂ የሰውና የሁኔታዎች ሰለባና መጫወቻ አትሁኑ!

መልካም ቀን!

Dr eyob