Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 89.19K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-30 11:24:45
ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
"በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?"
ልጁም አንገቱን ደፍቶ በአፍረት መለሰ፡-
አዎ.
ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"
ታዲጊው ልጅ:  በጣም ፈልጌው ነው
ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?
ልጅ፡ ምንም ገንዘብ አልነበረኝም።
ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችላለህ።
ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ።
ዳኛ፡ እና አንተ... ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?
ልጅ፡- የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ።
ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-
“ሌብነት በተለይም ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው።
ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ።
በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው 10 ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም.
ዳኛው ከኪሱ የ10 ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ።
"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል."
በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ።
ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።
ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።
13.0K viewsedited  08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 07:14:27 ልጆቻችሁን ሸጣችሁ ምን ገዛችሁ?
(አሌክስ አብርሃም)

ብዙ ወላጆችን  እያየሁ እና እየሰማሁ ልቤ ያዝናል! በተለይ  ልጆች ላላችሁ ሰዎች ከልቤ  ይህን እላለሁ! በዚች ምድር ላይ ለልጆቻችሁ ከእናተ ውጭ  ከልቡ ፍቅር የሚሰጣቸው፣ የሚያወሩት ጠቀመም አልጠቀመም የሚያዳምጣቸው፣ ከልቡ የሚያቅፉቸው፣ የሚስማቸው ፣  ሲያዝኑ መንፈሳቸውን ከፍ የሚያደርግላቸው ፣የሚያጫውታቸው ፣ከዳዴ እስከአዋቂነት ፣ ከዓለማዊ እስከመንፈሳዊው  ጉዞ መንገድ የሚመራቸው ፣  የሚያስተምራቸው፣ ከዚህ ክፉ ዓለም በፍቅር እና እንክብካቤ የሚጋርዳቸው ከወላጅ ውጭ ሌላ ሰው የለም! ወላጅ ከሆንክ ከሆንሽ እናንተ ብቻ ናችሁ ለልጆቻችሁ ያላችኋቸው! ወላ ዘመድ ወላ አስተማሪ ከእናንተ ቀጥሎ ነው! መቸም ደግሞ  የእናተን ሚና አይተኩም!

በተለይ አባቶች!...(በእናንተ ስለሚብስ) በሜካፕና በ"ላይት" ተብረቅርቀው ራሳቸውን ለገበያ የቀረቡ ሴቶችን የማይረባ ወሬና የወሲብ ስሜት የሚያነሳሳ ዳንስ ፣ ራቁትነት፣ ብልግና ፣ ቆሻሻ ጆክና ሀሜት ፣ ጥቅም የሌለው ጫጫታ ወይም ይሄን የሻገተ ፖለቲካ  ለማየት ቲክቶክ፣ ዮቲዮብ፣ ፌስቡክ ወዘተ ላይ ቀን ከሌት አፍጥጠህ ስትገለፍጥና ስትቋምጥ  ውለህ የምታድር አባት ...የምትከፍለው ተራ ካርድ ወይም የኢንተርኔት ሂሳብ ብቻ እንዳይመስልህ!  የልጆችህን ጊዜ ከፍለህ ቆሻሻ ትገዛለህ! ዱቄት በአመድ ትለውጣለህ!

እነዚህ  ሚሊየን ተመልካች ያላቸው ከንቱዎች ለመመልከት ከአንተ ሌላ ተመልካች የሌላቸው ልጆችህን ፊት ትነሳለህ! ፍቅር ትነሳለህ (እንደዛፍ ውሃ እያጠጣህ ስለተውካቸው ልጆች አደጉ አይባልም) ለልጆችህ እያንዳንዷ ሰዓት እያንዳንዷ ደይቃ የነገ እጣፈንታቸው ናት! በየደይቃው በየቅፅበቱ ነው ልጆች በአካልም በመንፈስም  የሚሰሩት! የረሳሀቸው ልጆችህ መረሳት የሚያመጣው የበታችነት ህመም ተጠቂ ይሆናሉ! ጊዚያቸውን ስትነጥቃቸው ከወላጅ ሊያገኙ የሚገባውን መብትና ፍቅር ትነጥቃቸዋለህ! ዛሬ የራካቸው ልጆች ነገ ይርቁሃል! ነገ በጣም ቅርብ ነው! ከስልክህ ቀና ስትል አድገው ታገኛቸዋለህ! ውድ ጊዜህን እንቅልፍህን ሰላምህን ሰጥተህ ስልክህ ላይ ለምታያቸው   ከነመኖርህ  እንኳን ለማያውቁህ የሶሻል ሚዲያ ርካሽ ነጋዴዎች ስትል ከአንተ ሌላ ማንም የሌላቸውን ልጆችህን ቤተሰብህን ትሸጣለህ! "ሊትራሊ" ልጆችህን ሽጠህ ነው የሆነች ቦዘኔ መቀመጫዋን ስታወዛውዝ  ለማየት በጊዜህ የምትገዛው፤በሆነ ሰው ቀልድ የምትገለፍጠው! በየቤታችሁ ያስገባችሁት ኢንተርኔት አጠቃቀሙ በወግ ካልተቃኘ  ልጆቻችሁን ደርድራችሁ በርካሽ  የምትሸጡበት ጉሊት ነው የሚሆነው!

እስኪ ወላጆች ራሳችሁን  ታዘቡ! ለቲክቶክ የምትሰጡትን ጊዜ ለልጆቻችሁ እየሰጣችሁ ነው? ወይስ ወደዛ ዝም እንዲሉ ቲቪ ወይ የሆነ ነገር ሰጥታችሁ ስልካችሁ ላይ ናችሁ? ለትዳር አጋሮቻችሁስ? ለወላጆቻችሁስ? ከቲክቶክ ፌስቡክ ምናምን ፋታ ብትውስዱ እንኳ አዕምሯችሁ የተሞላው በትርኪ ምርኪ ነውና ለልጆቻችሁ የምትሰጡት ደህና ሃሳብ እንኳን የላችሁም!  ስምህ የልጅህን ስም እየተከተለ እንደውሻ ስለጮኸ አባትነትህ ሙሉ ሆነ ማለት አይደለም! ያለህን ጊዜ ሁሉ ለቤተሰብህ ስጥ ፤የተረፉህን ልቅቃሚ ደይቃዎች ወደሶሻል ሚዲያው ወርውር! በቂ ነው! ልጅህን ቤተሰብህን ሸጠህ ቆሻሻ አትግዛ! በፈጠረህ ለሌሎች የላይክና ቪው ቁጥር ከመሆን ለቤተሰብህ አለኝታ ሁን! ባልታደለች አገር ተፈጥረው ያጡት ስፍር ቁጥር የሌለው ነገር ሳያንስ አንተም ተጨምረህ ልጆችህን የቲም አታድርጋቸው! ቆም ብለህ አስብ ከቤተሰቤ የነጠኩትን ጊዜ ምን ገዛሁበት በል? ምን ገዛህበት? አንችም እናት የሆንሽ  እንደዛው!

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
14.5K viewsedited  04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 12:06:44 ታላላቅ ጥቅሶችና ምክሮች

1.ትልቅ ሰውነት በዘር ወይም በትውልድ ሳይሆን በተግባራዊ ስራና በህይወት ፈተና ውስጥ ነጥሮ የሚወጣ ነው።

2.ከይስሙላ አንድነት ፣በእምነት ካልተዋቀረ ህብረት፣ በግርግር ከተሞላ መንጋነት ይልቅ ጥርት ያለ ልዩነት ለመፍትሄ ያበቃል።

3.በእውቀት ተመራምሮ አዲስ ነገር ማግኘት ለሰው ልጅ የስልጣኔ መጥረጊያ  መንገድ ከፋች ሲሆን የሀሰት ወሬ መፍጠር ግን የዝቅጠት መንገድ ነው።

4.ከሚጎትቱንና ከሚያደናቅፉን አሮጌ ችግሮች መውጣት ያሻናል፣አሮጌ ባላንጣዎቻችን በትላንት አባዚያችን ውስጥ እንድነቅዝ እንደሚሹ ማስተዋል አለብን።


5.ዋና ቀጣፊ ሰው ራሱን የሚያታልል ነው።

6.ገደልን የዘለለ ፈረስና ቂምን የተወ ሰው አዋቂ ነው።

7.የሚፈልገውን ያላገኘ ልብ ዘውትር መንገደኛ ነው።

8.ያለውን የማያውቅ የጎደለውን አያውቅም።

9.ጭንቀትህን በስራ ተካውና ተአምር ሲፈጠር ተመልከት።


10.ክፋት የአእምሮ በሽታ ሲሆን ቅንነት ግን የህሊና እረፍት ነው።

11.ሌሎችን ለመምሰል እንደሚመኝ ሰው ጭንቀት የበዛበት ሰው የለም።

12.ፍቅር የከንፈር ወይም የገንዘብ መገጣጠም ሳይሆን የልብ መገጣጠም ነው።


13.ቆንጮ ሴት ባየህ ጊዜ ተፈጥሮን አድንቅ እንጂ የዝሙት መንፈስ አይሰማህ። ዝሙት ከደካማ መንፈስ የሚመነጭ ነው።

14.ብዙ የሚናገሩ ሰዎች የማሰቢያ ጊዜ የላቸውም።

15.የማያውቀውን ነገር ያልተናገረ ጥበበኛ ነው።

16.ፍቅር በድንገት መጥቶ እንደሚያልፍ ጎርፍ ሳይሆን ጠልፎ የማያሰጥም የውቅያኖስ ማዕበል ነው።

17."ቅናት" ፍቅር እና ትዳርን ገዝግዞ የሚጥል ስለት ነው።

18.ሴቶች ጆሮዋቸውን ወንዶች አይናቸውን ያምናሉ።

19.ፍቅር የተፈጥሮ ሁለተኛ ፀሀይ ነው።

20.በፍቅር የተሞላች ቃል የወደቀን ሰው ታነሳለች።
 
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
12.7K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 16:16:34 አንዳንዴ . . . ያለ ነው!

አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!

አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!

አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!

አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!

አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!

አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!

አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!

አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!

አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
13.1K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-25 21:40:13 “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!”
ከአሌክስ አብርሀም
መፅሀፍ-አልተዘዋወረችም

በአገራችን ባህል የዝምታ ትርጉም ግራ የገባው ነው፡፡ እውነት በአደባባይ ሲደፈጠጥ እያዩ አፍን መሸበብ፤ ግን ደግሞ በስሚ ስሚ ለመጣ አሉባልታ ነፍስን ጭምር መስጠት። ጮኾ የማያወራ፣ ሐሳቡን የማይገልጽ ሕዝብ የሐሜት ጫካ ነው። በየጋራና ሸንተረሩ ጥይት ከማስጮኸ የበለጠ፣ ጮኽ ብሎ ያመኑበትን መናገር የሚከብደው ሕዝብ ጀግንነቱ ከባድ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በዝም አይነቅዝም ብሒል የነቀዘ ሕይወት እንመራ ዘንድ የፈቀድን ሕዝቦች መሆናችን ሳያንስ ይኽንንም ባህል አድርገን ልንኮራበት ይዳዳናል፡፡

ይኼ ተወልጄ ያደግሁበት ሕዝብ በሹክሹክታ ያወራል፣ ጓዳ ለጓዳ ያወራል፣ እውነት ይሁን ውሸት አግበስብሶ ያወራል፣ እንደ ወረርሽኝ ወሬ በብርሃን ፍጥነት ያዛምታል፣ በአደባባይ ግን ዝምተኛን ያደንቃል- ያበረታታል፡፡ በተረቱ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም” እያለ  ዝንብ ፈርቶ ዝም (እንዴት _ ለዝንብ ዝም ይባላል? ለምን ሰፈራችሁን አጽድታችሁ እንደልባችሁ አታወሩም? የሚል የማሪያም ጠላት ነው!) መንግሥትን ፈርቶ ዝም (እንዴት ዝም በሉ ለሚል መንግሥት ዝም ይባላል አፋኝ መንግሥት እጁን ከአፋችን ላይ እንዲያነሳ መንገር የለብንም ወይ? የሚል የአገር ጠላት ነው) ይሉኝታን ፈርቶ ዝም (እንዴት በይሉኝታ እንለቅ? ብንል የባህል ጠላት መባል ይመጣል፡፡)


ሁሉም ስሕተትና ፍርኃታችን እንደ ትልቅ ሐብት በእሳት ሰይፍ ተከቦ የሚጠበቅ ቅርስ ነው፤ እውነት ብቻ ነው ራቁት፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም እውነት የእብዶችና ሰካራሞች ልፈፋ ተደርጋ በየመድረኩ የምትሳለው፡፡ እብዶች እውነቱን እንዲናገሩለት “ጤነኛው' ከፍሎ ይታደማል፡፡ ይኼ ባህላችን ሲሆን ከያኒ የነፍሱን ጥሪ ጥሎ የጅሎች አፈቀላጤ ይሆናል፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምክንያት ፍርኃታችን ቢሆንም፣ ይኼንንም በሰበብ ስንጀቡነው (መቼም ሰበብ አናጣ) “ዝምታችን ትዕግስት የወለደው፤ ትዕግስታችንም አምላካችንን የምንፈራ ሕዝቦች ስለሆንን የተጎናጸፍነው ጸጋ ነው” እንላለን፡፡ እውነታው ግን አምላክን መፍራታችን ሳይሆን ፍርኃትን ማምለካችን ነው።

በዚህ ሁሉ ዝምታ ውስጥ የታቀፈ ጅልነት ድርጊት ሆኖ ሲፈለፈል ከግለሰብ እስከ አገር ስንት የጨነገፈ ኑሮ ፈጠረ!? ታዲያ የራሳችን ዝምታ ተጠራቅሞ ሲከብደንና አላራምድ ሲለን፤ በየዘመኑ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቅን በጋራ እንጮኻለን። የጨረባ ተዝካር! ይኼን ዓይነቱን ጩኸት አብዮት እንለዋለን (የታዘዙትን ሁሉ እሺ! እያሉ አብዮት አለ ወይ?!) ነገሩ ልክ ውሃ ውስጥ የተነከረ ውሻ፣ ውሃውን ከላዩ ላይ ለማራገፍ በደመነፍስ እንደሚርገፈገፈው ዓይነት ነው፤ ውሃው ቢራገፍም ውሻው ያው ውሻ ነው፡፡ አጯጯኻችን በአንድ ላይ በየአፋችን ስለሆነ ማንም ማንንም አይሰማም፤ ማንም የማይሰማው ጩኸት ደግሞ ከዝምታ እኩል ነው፡፡

ይኼ ዝምታ፣ የጅል ባንዲራ እንጂ ጨዋነት አይደለም። ባንዲራችን ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ለዘመናት በተከመረና በደደረ ጅልነታችን ላይ ይመስለኛል፡፡ የባንዲራችንን ቀለም እየጠቀስን የማንሰጠው ትርጉም የለም። ሁሉንም ቀለም እንደ ዳማከሴ ጨቅጭቀን ብንጨምቀው ከጀግንነታችንም በፊት፣ ከኩሩነታችንም በፊት፣ከአገር ፍቅራችንም በፊት የሚንጠባጠበው ጅልነታችን ሳይሆን ይቀራል?!

እሱን እየተቀባን ስንት ጊዜ ከዘመን በሽታ ተፈወስን ብለናል?! ፈውሳችን ሐሰት ነበርና ምስክርነታችን የታተመበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ብዙዎች በነጠላም በጅምላም የጅል በትር ሰለባ ሆነው ወደ መቃብር ወርደዋል፡፡


የተረፍነው እንዴት ተረፍን? እያልኩ ሳስብ፣ አንዳንዶች “ምሕረቱ በዝቶልን'' ቢሉም እኔ ግን ፈጣሪም ከዚህች ከኛ ምድር በተዋሰው ተረት “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ብሎ ለአጫዋችነት ትቶን ይሆናል እላለሁ፡፡ አገሬ ጨዋታና ተጨዋች ይበዛታል፡፡ እንደ አገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን? እስከምል ድረስ የአገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡

ጅልነቴ ከሕዝብ ባሕር የተቀዳ ነው ስል፣ ለጥፋቴ ሌላ የሕዝብ ክንብንብ ውስጥ መደበቄ አይደለም፤ ምንስ ቢሆን ሕዝብ የሚባለው አጀብ ለሚሊዮኖች ቢሰነጣጠር አንዱ ስንጣሪ መሆኔ አይቀር፡፡ ሕዝባዊ ጀግንነት፤ ሕዝባዊ ታሪክ እንዳለ ሁሉ ከየቤታችን አዋጥተን አገራዊ ያደረግነው ሕዝባዊ ጅልነት አለመኖሩን ማን አጥንቶ ነገረን?! ጅልነት ቀለም ነው፤ ታሪካችን እኛም በግልና በጅምላ አማርን ብለን የተቀባነው የተኳኳልነዉ ጠይም ቀለም፡፡ በዚህ ጠይምነት በኩል ስለተገለጠ ግለሰባዊ ጅልነቴ በጸጸት አወራለሁ... በጓዳዬ ለአገር ያዋጣሁት የጅልነት ድርሻ... ይኽም ከንስሓ ይቆጠር እንደሆን እንጃ፡፡

@zephilosophy
@zephilosophy
12.6K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-17 21:39:59 ጣፋጩ ገዳይ መርዝ!

በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።

ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።

ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር።

ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል

@Human_Intelligence
13.1K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-09 07:35:04 የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

ሕይወታችንን ማስመለስ ማለት በአጭሩ ሲተረጎም በአንድ ሰው፣ ሁኔታ ወይም ልምምድ ምክንያት ከደረሰብን ቀውስ የተነሳ በትክክል ማሰብ፣ መስራት፣ መተኛትም ሆነ መኖር እስከማንችል ድረስ የደረሰውን ሁኔታችንን እንደገና ወደቀድሞው ጤናማ ሁኔታ ማስመለስ ማለት ነው፡፡

•  የጎዳችሁና እስክትበቀሉት ድረስ ውስጣችሁን የሚያናድደው ሰው የወሰደባችሁን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  ሰዎችን አምናችሁ በተወሰደባችሁ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ምክንያት ዘወትር ከመቆጨታችና ከመቆዘማችሁ የተነሳ የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

•  አፍቅራችሁ ትንሽ ከተጓዛችሁ በኋላ ያ ሰው ለእናንተ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ብትደርሱበትም ካላችሁ የስሜት ትስስር የተነሳ ልትረሱት ባልቻላችሁት ሰው የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!  

•  ማንኛውንም ሰውም ሆነ ሁኔታ ከመፍራታችሁ የተነሳ ወደፊት መራመድ እስከማትችሉ ድረስ በመሆናችሁ ምክንያት የተወሰደውን ሕይወታችሁን አስመልሱ!

ወደራሳችሁ ተመለሱ! ወደቀደመው ሰላማችሁ ተመለሱ! ወደእውነተኛው ማንነታችሁ ተመለሱ! ከምንም ሁኔታና ከማንም ሰው ጫና ውጪ ወደነበራችሁበት ሚዛናዊ ሕይወት ተመለሱ!

ንቁ! ወስኑ! ምክርና እገዛን ፈልጉ! የድሮውን ጤናማ ማንነታችሁን እንደገና የራሳች አድርጉ እንጂ የሰውና የሁኔታዎች ሰለባና መጫወቻ አትሁኑ!

መልካም ቀን!

Dr eyob
12.9K views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-18 22:35:48 #የተፈጥሮ_ዑደት

በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ ድል ማድረግም ሆነ ድል መሆን የሚባሉ ነገሮች የሉም። ያለው እንቅስቃሴ ብቻ ነው:: ክረምት ከሁሉም የበላይ ሆኖ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ ይጣጣራል:: ሆኖም ጊዜውን ጠብቆ የፀደይን ተተኪነት ከመቀበል በቀር አማራጭ አይኖረውም፡፡ ፀደይም አበቦችን እና ፍካትን እንዲሁም ደስታን ይዞ ከተፍ ይላል። በጋውም ቢሆን ሞቃታማ ቀናቱን ለዘለዓለም ለማዝለቅ መውደዱ አይቀርም:: ነገር ግን የበልግን መምጣት ተቀብሎ ስፍራውን አስረክቦ ዘወር ይላል:: በልግም ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ እድል ይሰጣታል::

አጋዘን ሳርን ብትበላም እርሷ ራሷ የአንበሳ ምግብ ናት:: ይህ የጥንካሬ ጉዳይ አይደለም:: ማን ይበልጥ ይበረታል ስለማለትም አይደለም:: ይልቁን አምላክ የሞትንና የትንሳኤን ዑደት ለእኛ የሚያሳይበት መንገድ ነው:: በዚህ ዑደት ውስጥም አሸናፊም ተሸናፊም የለም:: መታለፍ ያለባቸው ደረጃዎች ብቻ እንጂ። የሰው ልጅ ልብ ይህንን እውነታ ሲረዳ ነፃ ይሆናል፤ አስቸጋሪ ወቅቶችን ለማለፍ አያዳግተውም፤ በድል አድራጊነት የሞቅታ ስሜትም አይታለልም:: ሁለቱም አላፊ መሆናቸውን አይዘነጋም:: አንዳቸው በሌላቸው ይተካሉ::

ዑደቱም ይቀጥላል::

ስለዚህ የፍልሚያ ቀለበት ውስጥ ያለ ቡጢኛ (የራሱ ምርጫ አሊያም ሊመረመር የማይችል እጣ ፈንታ እዚያ ያስገኘው) ከፊት ለፊቱ በሚጠብቀው ፍልሚያ ተስፋ በደስታ ስሜት ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፡፡ ክብሩንና ግርማውን መጠበቅ ከቻለ ፍልሚያውን ቢሸነፍም እንኳ ተሸናፊ ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም መንፈሱ ምንም አልተሸራረፈምና።

ስለደረሰበት ነገር ሁሉ ሌሎችን መውቀስን ሙጥኝ አይልም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍቅሮ፤ የፍቅር ጥያቄው ውድቅ ከተደረገበት
ጊዜ አንስቶ ይህ ውድቀት በእርሱ የማፍቀር ችሎታ ላይ ያመጣው አሉታዊ ለውጥ እንደሌለ ያውቃል::

በፍቅር ውስጥ እውነት የሆነው ሁሉ በጦርነት ውስጥም ይሰራል።

ፓውሎ ኮሆልዮ
@Human_Intelligence
16.8K views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-14 21:45:39 አክሱም ላይ አንቀላፍቶ
ማይጨው ላይ መንቃት
የቀጠለ

ነገርግን አክሱምን፣ ላሊበላን፣ ፋሲልና ጀጎልን የጠረቡ እጆች ስለምን ለሺህ ዘመናት በደሳሳ ጎጆዎች ውስጥ እንደተቸነከሩ ማሰብ ሕመምን ይፈጥራል፡፡ ፊደል ነበረን፤ እንደ ሕዝብ ከመጻፍ ይልቅ መስማትን እንመርጣለን፡፡ ይበልጡኑ መሀይማን ነበርን፡፡ በኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ሙዚቃን በኖታ በመጻፍ የመጀመሪያዎቹ ብንሆንም እዚሁ አበርክቶ ላይ ጥቂት ሀሳብ ለመጨመር የተክሌ አቋቋም, እስኪቀመር አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት መጠበቅ ነበረብን፡፡

በ1237 ዓ.ም አካባቢ ከሦስት መቶ ዘመናት የዛግዌያን አገዛዝ በኋላ ሥልጣን በቤተክርስቲያን ጠንካራ ተጽዕኖ ከዛግዌ ነገሥታት ወደ የዘር ሀረጋቸውን ከሰሎሞን ዘር እንመዛለን ለሚሉ ሰሎሞናዊ ነገሥታት ተዛወረ፡፡ የዛግዌ ነገሥታትን ሥልጣኑን ለሰሎሞናዊው ገዥ ይኩኖአምላክ እንዲያስተላልፉ በመወትወት፣ በመገሰጽ አቡነ ተክለኃይማኖት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል፡፡
በሂደቱም ቤተክርስቲያን እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ድረስ የዘለቀ የክፍለዘመናት የሢሶ መንግሥትነት ፈላጭ ቆራጭነቷን አጸናች፡፡

ጥቂት ቆይቶ በ330 ዓ.ም አካባቢ የሰሎሞናዊ ስርወመንግሥቱን በትርክት እና በሕግ ለማጽናት ሲባል ‹ክብረነገሥት› የተሰኘው መጽሐፍ የመጻፉ አስፈላጊነት ታመነበት፡፡

መጽሐፉ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ ሥልጣን ባለቤቶች የዘር ሀረጋቸውን ከንጉሥ ሶሎሞን እና ከቀዳማዊ ምኒሊክ ዘር የሚመዙ ብቻ መሆናቸውን በማያሻማ ኹኔታ ይደነግጋል፡፡ በዚህም መጽሐፍ የተነሳ ኢትዮጵያን ሀገራቸውን እንደዳግማዊት ኢየሩሳሌም እንዲመለከቷት ተበረታተዋል፡፡ ለዘመናት በክርስትና እምነት መነሻነት በተገነባው በዚህ ትርክት እና በክርስትው ኃይማኖት ምክንያት ከኢትዮጵያ ውጭ በኢትዮጵያዊያን (በሰሜነኛው ክርስቲያን) አዕምሮ የታተመች ሌላ ከተማ (ሀገር) ብትኖር ኢየሩሳሌም ብቻ ናት፡፡ በዚህ ሰበብ ይመስላል ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ከውጭው ዓለም የመጣውን ሰው በተለይ ክርስቲያኑን ሁሉ የኢየሩሳሌም ሰው እንደሆነ ይቆጥሩ እንደነበር በልዩ ልዩ ተጓዦች ማስታዎች ላይ ተዘግቧል፡፡

በዚህ መልኩ በአስራ አራተኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ የተጻፈው ክብረነገሥት ከፊውዳል ሥርዓቱና ከቤተክህነቱ ጋር ተቀይጦ በኢትዮጵያ የሥነ መንግሥት ታሪክ ሰባት መቶ ዘመናት ድረስ የዘለቀ ገዥ ትርክትን ፈጠረ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከሞላ ጎደል በአንድ አገዛዝ ሥር የሚያድር፣ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን የሚናገር በአብዛኛው የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነውን ሰሜነኛ ሕዝብ ለሰባት ክፍለዘመናት ያስተዳደረ መሪ ትርክት ሆኖ አሳለፈ፡፡ ዳግማዊ ምንይልክ የተበታተነውን የዳር ሀገር ሕዝብ ሁሉ በአንድ አጠቃለው በዘውዳዊ ሥርዓቱ ሥር ካስገቡትም በኋላ በዚህ ትርክት ሥር እንዲመላለስ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የሰመረ ነበር ባያስብልም ቢያንስ በእሳቸው ዘመን ትርክቱ የአንድነት ስሜት በመፍጠሩ የአድዋ ጦርነትን የመሰለ በተባበረ ከንድ የተገኘ እጅግ አንጻባራቂ ገድል ለመከወን መሣሪያ ሆኗል፡፡

ኢጣሊያኖች ኢትዮጵያን ዳግም የወረሩ ሰሞን በቅኝ ገዥ ሴራ ሕዝቡን ለመከፋፈል አማርኛ ተናጋሪውን ሕዝብ በጅምላ የፊውዳል ሥርዓቱ ተጠቃሚ እና ጨቋኝ ገዥ መደብ እንደሆነ ፈርጀው ትርክታቸውን ማጠንጠን ጀመሩ፡፡ ይህ ትርክት በተለይ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ድፍን ሃያ ሰባት ዓመታት በሕገመንግሥት፣ በመንግሥት በጀት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃናት በይፋ እና በስውር እንደ አስፈላጊነቱ ይቀነቀን ነበር፡፡ በበኩሌ ሰሜነኛው ሕዝብ ለፊውዳል ሥርዓቱና ለአገዛዙ በነበረው ጂኦግራፊያዊ ቅርበት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ በተለዬ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ ከሁሉም በላይ በሥርዓቱ ይበደል እንደነበር አስባለሁ፡፡

ከ2010 ዓ.ም በኋላ የመጣው አስተዳደር በመደመር ግራ የገባው ቅኝት እዚያ እና እዚህ እየረገጠ ምንም የትርክት ለውጥ ሳያስፈልገው የጨቋኝ ተጨቋኝ የትርክት ንጥቂያ እና ቁማርን ማስቀጠሉን ለመረዳት ብዙ የፖለቲካ ብስለት የሚጠይቅ አይመስለኝም፡፡

እኛ ግን ለመላው ጥቁር ሕዝብ ትርክት ቀማሪነት የታጨን ሆነን ሳለን የራሳችን የቤት ሥራ እንኳን ሰርተን ያልጨረስን መሳቂያ የመሆናችን ነገር ያሳዝናል፡፡ ታላቁ ጥቁር የተሰኘ በንጉሴ አየለ ተካ የተጻፈ መጽሐፍ ያነበበ ሰው ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ አጼ ኃይለሥላሴ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ለነበሩ ጥቁር ሕዝቦች ሁሉ እንደምን ይታገሉ እንደነበር መታዘብ ይችላል፡፡

ታሪካችንን አላወቅነውም፡፡ መናናቂያ አድርግነዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘነውን በሰው ዘርን ሁሉ ፊት በግርማ ሊያስጠራን የሚችል ዕድል እንደዘበት አምልጦናል፡፡ እናስ ያቆሙን መሰረቶች ምን ያህል ጽኑዓን ነበሩ? እንደ ኅብረተሰብ የአቋራጩ፣ ልክፍተኞች ሆነን ለመገኘታችን ምክንያቱ ምንድን ነው? የምንዋቀሰው፣ የምንናናቀው በድንቁርናችን ልክ አይደለምን? ለፍጥረት ሁሉ ከሚተርፍ በረከት፣ ኅሊና እና ርህራሄ ጋር ተፈጥረን ሳለን ዘመኑን ስላለመዋጀታችን በሰንደቅ ዓላማ ለሚያስለምን ችጋር ራሳችንን አላጨንምን?

ይቀጥላል
ደራሲ-ያዕቆብ ብርሀኑ
መፅሀፍ-በፍም እሳት መቃመስ
14.9K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 12:14:34
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።
13.3K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ