Get Mystery Box with random crypto!

እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተወጣጣህበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!! በአንድ ወቅት አንድ ገ | የስብዕና ልህቀት

እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተወጣጣህበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!!

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ወስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።

ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን  አዘነች፡፡

ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ ከዚያም በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች። በሒደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡ በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡

ውድ አንባቢያን እንደሚታወቀው የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር ደግሞ በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡ አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡

በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡

ውድ አንባቢያን በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው! በየጊዜው ሊገጥመን የሚችለውን ችግር ልክ እንደ አህያዋ የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው ሁሉ አንተም/አንቺም በየጊዜው የሚገጥማችሁን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀማችሁ በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልጋል፡፡ ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው።
በመሆኑም ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ ተጓዙ ለማለት እወዳለሁ።

#share
Join: @Human_Intelligence