Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት እንደሚያስከፍል አስታወቀ! ሳፋሪኮም ኢ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት እንደሚያስከፍል አስታወቀ!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለጀመረወው አገልግሎቶች ስንት እያሰከፈለ ነው በሚል ከአል ዐይን ለቀረበለት ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።

ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው።

ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአል ዐይን አስታውቋል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media