Get Mystery Box with random crypto!

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በድብቅ ከደብረጺዮን ጋር መነጋገራቸው ተነገረ። አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተ.መ.ድ ህ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በድብቅ ከደብረጺዮን ጋር መነጋገራቸው ተነገረ።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተ.መ.ድ ህግ ጥሰው በኢትዮጵያ በአሸባሪነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር በድብቅ አጭር ግንኙነት ማድረጋቸው ይፋ ሆኗል።

የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ሾልኮ የወጣ ኢሜል አስመልክቶ ለጋዜጠኞች እንዳረጋገጡት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባለፈው ሳምንት ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ጋር “ለአጭር ጊዜ” መነጋገራቸውን አምነዋል። ጉተሬዝ በምን ጉዳይ ላይ የተ.መ.ድን አሰራር የጣሰውን ንግግር ከህወሓት መሪ ጋር እንዳደረጉ ግን በግልጽ አልተናገሩም።

ንግግሩ በኦገስት 25 ቀን 2022 መደረጉን ዱጃሪክ በይፋ አምነዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሪ ከአሸባሪ ድርጅት ጋር በቀጥታ መደራደሩ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ ሲሆን ወያኔ አሁንም በአሜሪካ መንግስት እና በአፍሪካ ቀንድ በህግ ሽብርተኛ ከባሉት ቡድኖች ውስጥ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። በአሰራሩ መሰረት የተባበሩት መንግስታት ከአይኤስ፣ ከአልሸባብ፣ ከአይአርኤ ወይም ከቦኮ ሃራም ጋር በቀጥታ እንደማይገናኝ ሁሉ ከሽብርተኛው ህወሓት ጋርም መገናኘት አይገባውም ነበር ተብሏል።

ከዚህም ባሻገር በጓተሬስ በኩል የተወሰደው መሰል እርምጃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር አንቀጽ 51 ላይ የተቀመጠው ቀጥተኛ ህግ እንዲሁም የተ.መ.ድ አባል ሀገራት ራሳቸውን ከሽብርተኝነት የመከላከል እና አስፈላጊ ከሆነም ጎረቤቶች እና አጋሮች እንዲረዷቸው የመጠየቅ መብት የሚሰጣቸው አንቀጽ የሚቃረን ነው።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ላይ የትጥቅ ጥቃት ከተፈፀመ የፀጥታው ምክር ቤት አለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን እርምጃዎች እስካልወሰደ ድረስ በዚህ ቻርተር ውስጥ ያለው ማንኛውም ነገር የግለሰብም ሆነ የጋራ ራስን የመከላከል መብትን መጉዳትም አይፈቅድም። ይህንን ራስን የመከላከል መብትን በመጠቀም አባል ሀገራት የሚወስዱት እርምጃ ወዲያውኑ ለፀጥታው ምክር ቤት ሪፖርት ይደረጋል። ይህም ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ ወይም ወደነበረበት ለመመለስ አስፈላጊ ነው እርምጃ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተ.መ. ድ በሀሙስ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ዱጃሪች የወያኔን 12 የነዳጅ ታንከሮች የዘረፉትን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞችን ጥቃት ወይም አፈና እንዲሁም የአማፂያኑ ቀጣይ የህጻናት የግዳጅ ምልመላ ጉዳይ ጉዳይ ሳይላይ ሳይናገሩ እንዳለፉት ይታወሳል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media