Get Mystery Box with random crypto!

በቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቢሮ ኃላፊ የባንክ አካውንት፤ 8.5 ሚሊዮን ብር ገቢ ተደርጎ እንደ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቢሮ ኃላፊ የባንክ አካውንት፤ 8.5 ሚሊዮን ብር ገቢ ተደርጎ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ

ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ለሚገኙት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቢሮ ኃላፊ፤ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ 8.5 ሚሊዮን ብር በባንክ አካውንታቸው ገቢ እንደተደረገላቸው የፌደራል ፖሊስ ገለጸ። በዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ ስም ከተከፈቱ አራት የባንክ አካውንቶች፤ 6.4 ሚሊዮን ብሩ ወጪ መደረጉንም አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ይህን የገለጸው “በስልጣን አላግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል” ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በሚገኙት ዶ/ር ሙሉቀን ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን ዛሬ ሰኞ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ባቀረበበት ወቅት ነው። ፖሊስ በተጠርጣሪው ስም በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች የተደረጉ ዝውውሮችን መረጃ ያገኘው ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት መሆኑን የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን እየተመለከተ ለሚገኘው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል።(Ethiopian insider)

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media