Get Mystery Box with random crypto!

ህወሃት ግብአተ መሬቱ እስኪረጋገጥ ድረስ እንቅልፍ እንደሌለዉ የሲዳማ ክልል ገለፀ። ትዕግስትንና | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

ህወሃት ግብአተ መሬቱ እስኪረጋገጥ ድረስ እንቅልፍ እንደሌለዉ የሲዳማ ክልል ገለፀ።

ትዕግስትንና የሰላምን ጥሪ ላልተቀበለዉ የህወሓት ቡድን ግብአተ መሬቱ እስኪረጋገጥ ድረስ የሲዳማ ህዝብና መንግሥት እንቅልፍ እንደለሌዉ ክልሉ አሳወቀ።

ሲዳማ ክልል በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ባወጣዉ መግለጫ ህወሃት ሀገር ለማፍረስ ወደ ኋላ የማይል በጥላቻ የታወረ ቡድን ነዉ ያለ ሲሆን በሀገራችን ላይ በተደጋጋሚ ጦርነት ከፍቷል ይህም ለሰላም ምንም አይነት ቦታ የሌለው ለሐገርና ለህዝብ ጠንቅ ተልዕኮ ማንገብን አመላካች ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ዳግም ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት በመክፈት ለኢትዮጵያና ለንፁሃን የትግራይ ህዝብ ያለውን ንቀት አሳይቷል ብሏል መግለጫው ።

የክልሉ መንግስት በመግለጫዉ እንዳመላከተዉ ከስህተቱ የማይማረው ህወሓት ዳግም ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያለውን ጥላቻ ያሳየበት ነው ሲል ገልጿል። ይህም ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጣ የሚያነሳሳና በተባበረ ክንዳቸው ህወሓትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግባተመሬቱ እንዲያፋጥኑ የሚያደርግ መሆኑን ገልጧል ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media