ከደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማው ሰላም እና ደህንነት ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም ፦
- የምግብ ቤቶች ፣ የምሽት መጠጥ ቤቶች/ግሮሰሪዎች/ ከምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ተከልክሏል።
- ማንኛውም ምርት ላይ የዋጋ ጭማሬ የሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።
- በመፈናቀል ሆነ በሌላ ማንኛውም ምክንያት ወደ ደሴ ከተማ የገቡ ተፈናቃዮች የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል የፀጥታ ኃይሎች ለጋራ ደህንነት ለሚተገብሯቸው የፍተሻና የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎች ተባባሪ የመሆን ግዴታ አለባቸው ተብሏል።
- አልጋ ቤት፣ የመኖሪያ ቤት ወይም መደብ ቤት አከራዮች የየትኛውንም ተከራይ ማንነትን የሚገልፅ መረጃ ለፀጥታ ተቋማት የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
- ወደ ደሴ በማንኛውም ምክንያት የገቡ እንግዶች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- ከተፈቀደላቸው የከተማው የፀጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል።
- ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም የከተማችን ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 /ሁለት/ ሰዓት ጀምሮ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- በከተማ ደረጃ እውቅና ያላቸው የተሰጣቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ብቻ ህዝቡን እንዲያገለግሉ ተወስኗል።
- በሁሉም አካባቢወች የሚገኙ ባጃጆች እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።
- የDSTV አገልግሎት መስጫዎች ፣ በጋራ ተሰብሰቦ ጫት የሚቃምባቸው መቃሚያ ቤቶች ፣ የሽሻ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በይፋም ሆነ በስውር አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።
(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)
@Hulaadiss