Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች የጀመረውን ወረራ እንቀለብሳለን ሲል የደቡብ ክልል ገለፀ። የ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች የጀመረውን ወረራ እንቀለብሳለን ሲል የደቡብ ክልል ገለፀ።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች የከፈተዉን ጦርነት
በተባበረ ክንድ ለመቀልበስ ዝግጁ መሆኑን አሳዉቋል።

ክልሉ በዛሬዉ ዕለት ባወጣዉ መግለጫ  ከሰላም ይልቅ ጦርነትን መርጦ የሀገርን ሉዓላዊነት ለመዳፈር አልሞ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የህወሓት ቡድን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል ለመመከት  ዝግጁ መሆኑን ገልጧል።

መንግስት በሽብርተኛ እያለ የሚጠራዉ ህዘሓት ነእኔ ያልመራኋት ሀገር መፍረስ አለባት በሚል እሳቤ ለሰላም የተዘረጋውን አማራጭ ወደ ጎን በመተው ለጋ ህጻናትን በማሰለፍ ግልጽ ወረራ መጀመሩን ያሳወቀው መግለጫዉ    በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ ከፈጸመው ክህደት ጀምሮ የትግራይ ወጣቶችን ወደ ጦርነት በማስገባት በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ግልጽ ጦርነትና ወረራ ያደረሰው እልቂት  ቡድኑ ለሰብዓዊነት ምንም የማይራራ አረመኔ መሆኑን በግልጽ የማያሳይ ነዉ ብሏል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media