Get Mystery Box with random crypto!

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን በጀት መመደቡን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳደሩ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያለበትን ደረጃ ቦታው ድረስ ሄደው መመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የስታዲየሙን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት አጠናቆ በአህጉር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን ለማድረግ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን የማጠናቀቂያ በጀት መድቧል ነው ያሉት፡፡

የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናቆ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ዶክተር ይልቃል ጨምረው ገልጸዋል።(Ethiofm)

የሁሌ አዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
Facebook : https://www.facebook.com/HulaadissEth
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media?