Get Mystery Box with random crypto!

በጀሞ አንበሳ ገራዥ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ የአንድ ሰው ህይወት አልፎ ተገኘ። በአዲስ አበ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በጀሞ አንበሳ ገራዥ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ የአንድ ሰው ህይወት አልፎ ተገኘ።

በአዲስ አበባ ዛሬ በሚገባደደዉ ሰኔ ወር ዉስጥ ብቻ አምስት ሰዎች ወንዝ ውስጥ በመግባት ህይወታቸዉ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ጀሞ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ እሮብ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ አንድ የ35 ዓመት ወጣት ወንዝ ዉስጥ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን እና አስክሬኑ መዉጣቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ነጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በሰኔ ወር ወንዝ ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉን ካጡ ሰዎች መካከል ሁለት ታዳጊዎች ኳስ ለማውጣት በሚል ወንዝ ውስጥ የገቡ እና አንድ ታዳጊ ለመዋኘት በሚል ነበር፡፡በተጨማሪም በተያዘዉ ሳምንት ሁለት ሰዎች ወንዝ ዉስጥ ገብተዉ ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን የአሟሟታቸዉ ሁኔታ ተመሳሳይ በመሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል፡፡የተያዘው የክረምት ወቅት እየጣለ ያለዉ ዝናቡ ከፍተኛ በመሆኑ ከጎርፍ ጋር ተያይዞ የሚደርሰዉ የሞት መጠን እየጨመረ እንደሚገኝ በማንሳት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

የሁሌ አዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ፤
Facebook : https://www.facebook.com/HulaadissEth
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media?