Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከዚህ ቀደም በ70/30 በማህበር ለመደ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከዚህ ቀደም በ70/30 በማህበር ለመደራጀት ተመዝግባችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች  ከሚያዝያ 8/2016 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ  6ኛ ፎቅ የጋራ መኖሪያ እና ህብረት ስራ ማህበር ዳይሬክቶሬት ዘውትር በስራ ሰአት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ቀደም ሲል 70 ፐርሰንት በባንክ አካውንት ገንዘብ አስገብታችሁ ከሆነ የባንክ እስቴትመንት ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ 70 ፐርሰንቱን ገቢ ያላደረጉ ከሆነ ለተመዘገቡበት የቤት አይነት ከሚያዝያ 8/2016 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በቀድሞ የ40/60 ወይም የ20/80 ቤት ቁጠባ አካውንት ላይ ገቢ በማድረግ  እና እስቴትመንት ይዛችሁ በመቅረብ ብቁ መሆኑን በአካል ቀርበው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡