የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የነበረዉን ደንብ በመሻር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ለሚሰጣቸው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል ። የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አዲሱ ደንብ ከመዉጣቱ በፊት ሲሰራበት የነበረዉን የሰነዶች ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያን በመሻር ማሻሻያዉ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያ ለመወሰን ባወጣዉ በዚህ ደንብ በተቀመጠው አዲሱ የክፍያ መጠን የሰነድ አይነቶቹ ቢለያይም ለሁሉም አገልግሎቶች ከ 200 ብር ጀምሮ እስከ 500 ብር ድረስ ክፍያን ይጠይቃል ። ካፒታል በተመለከተዉ በዚህ ደንብ ላይ ለሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ዉል ሰነድ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ሽያጭ ፣ ለመመስረቻ ፅሁፍ ሰነድ እና በስጦታ መልክ ለሚሰጡ ንብረቶች ዉል ሰነድ የክፍያ አገልግሎት ተመን ከወጣላቸው መካከል ዉስጥ ተካተዋል። 13.3K views12:55