Get Mystery Box with random crypto!

ላለፉት 23 ዓመታት የይገባኛል ክርክር የነበረበት ቤት ክርክሩ ሳይቋጭ በኮሪደር ልማት ምክንያት ፈ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ላለፉት 23 ዓመታት የይገባኛል ክርክር የነበረበት ቤት ክርክሩ ሳይቋጭ በኮሪደር ልማት ምክንያት ፈረሰ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ባረጋገጠው መረጃ መሰረት ይህ ቤት ይገኝ የነበረው ቦሌ ወሎ ሰፈር ወደ ቄራ መታጠፊያው መንገድ አካባቢ ላይ ነበር፡፡

ይህን ቤት ሁለት ግለሰቦች የይገባኛል ጥያቄ አንስተው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤትም ወስደውት ላለፉት 23 ዓመታትም ክርክሩ በሂደት ላይ ነበር ተብሏል፡፡

ክርክሩ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ሊወስድ ቻለ በሚል ኢትዮ ኤፍ ኤም ላነሳው ጥያቄ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የህግ ባለሙያ ጉዳዩ በእርግጥም ውስብስብ ችግሮች እንደነበሩበት ነግረውናል፡፡

የክስ ሂደቱ መቋጫ ሳያገኝ የተንዛዛው ይህ ክርክር አሁን ላይ በኮሪደር ልማት ምክንያት ቤቱ መፍረሱን ከህግ ባለሙያዎች ማረጋገጥ ችለናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8