Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የአገሪቱን የንግድ ባንኮች ባላቸውን ካፒታልና አሴት መሰረት በሶስት የተለ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የአገሪቱን የንግድ ባንኮች ባላቸውን ካፒታልና አሴት መሰረት በሶስት የተለያዩ ምድቦች መክፈሉ ተገለፀ።
እንደ መረጃ መንጮች የአገሪቱ ባንኮች ከፍተኛ ምድብ፣ መካከለኛ ምድብ እና ዝቅተኛ ምድብ በማለት ተከፍለዋል ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአገሪቱ ጠቅላላ ባንኮች 49.5 በመቶ የሃብት መጠን እንዲሁም 48.7 በመቶ የተቀማጭ ገንዘብ በመያዝ ከፍተኛ ምድብ ላይ መቀመጥ እንዲችል የተደረገ ሲሆን ሌሎች አምስት ባንኮች በድምር ከአገሪቱ ጠቅላላ ባንኮች 28 በመቶ የሃብት መጠን እንዲሁም 29.4 በመቶ የተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰብ መካከለኛ ምድብ ተቀምጠዋል።
በዚህ ደረጃ የተመደቡ ባንኮች አቢሲኒያ ባንክ ፣ ዳሽን ባንክ፣ሕብረት ባንክ ፣ አዋሽ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሲሆኑ የካፒታል መጠናቸው በድምር ባለፈው ሰኔ 2023 በጀት መዝጊያ ላይ 31 በመቶ መሆኑ ተገልጿል ።

በዝቅተኛ ምድብ የተቀመጡት 24 ባንኮች ሲሆኑ 22.5 በመቶ የሃብት መጠን እንዲሁም 21.9 በመቶ ተቀማጭ ገንዘብ አላቸው የካፒታል መጠናቸው ከጠቅላላው የአገሪቱ ባንኮች 41.6 በመቶ መሆኑ ተገልጿል ።