Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ መልሳ ልትገነባ ፈራርሳለች እዚህም እዚያም መንገድ ፣በመንገድ ላይ የተተከለው ዛፍ፣ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

አዲስ አበባ መልሳ ልትገነባ ፈራርሳለች

እዚህም እዚያም መንገድ ፣በመንገድ ላይ የተተከለው ዛፍ፣ የንግድና የመኖሪያ ቤት፣ ህንፃውና አጥሩ ሳይቀር ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ከሰሞኑን ሸገር ስቱዲዮ ተገኝተው ስለ ጉዳዩ ሲያብራሩ ለተነሺዎች ከ7 ወር በፊት መረጃ ሰጥተናል፤ በተለያየ ምክንያት ያልሰሙ ካልሆኑ በስተቀር ሌሎቹ ስለ ጉዳዩ በቂ መረጃ ነበራቸው ሲሉ መልሰዋል፡፡

መንግስት አስቤና መክሬ ስራውን ጀመርኩኝ ቢልም የሚታየው ግን ከዛ የተለየ ነው፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተገነቡ፣ ከቀናት በፊት የተተከለው፣ የተገነባና የተቀባው ሁሉ ዛሬ ፍርስራሽ ሆኗል፡፡

ይህ በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ምንድነው?

የእለት ጉርሱን ተሯሩጦ የሚያገኘው ኢ-መደበኛ ስራ ላይ የተሰማራው የከተማው ህዝብስ በዚህ የማፍረስ መገንባት፣ የመኖሪያ ቦታውን የመቀየር ሒደት ምን ያህል ተጎጂ ነው?





ተህቦ ንጉሴ